ለአንተ ጌታ
Lante Gieta
1998 · ትራክ 9 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ለአንተ ጌታ አያቅትህም
ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
፩) ግራ ቀኝ ለሚል ጭንቀት ለያዘው
ፈውስን ፈልጐ በለቅሶ ላለው
ደርሶ የሚፈውስ የሚታደገው
ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ነው
አዝማች · Chorus
ለአንተ ጌታ አያቅትህም
ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
፪) በገዢ ቁጣ ልቡ ለራደ
ስፍራውን ሲለቅ ሸርተት ላለ
የንጉሥ ልቡ በእጁ ይሆነው
አጽንቶ የሚያቆም መድሃኒያለም ነው
አዝማች · Chorus
ለአንተ ጌታ አያቅትህም
ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
፫) በባዕድ ምድር በእስር ላለ
ተስፋዬ አሁንስ ማን ነው ለሚለው
የእስራአኤል ብርታት ረዳት የሆነው
እስረኛን ፈቺ እግዚአብሔር ነው
አዝማች · Chorus
ለአንተ ጌታ አያቅትህም
ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
፬) በሰማይ በምድር የሌለው መሳይ
ለተዋረደ ክብርን የሚያሳይ
እንደ ኢየሱስ አረ ማን አለ
ሁሉንም መስራት ማድረግ የቻለ
አዝማች · Chorus
ለአንተ ጌታ አያቅትህም
ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
፭) እጅህ ስትሰራ ማየት ለጓጓው
ተነስ እያለ ፊትህ ላነባው
በእሳት መልሰህ ታሳየዋለህ
ጠላቱን ጌታ ታሳፍራለህ
አዝማች · Chorus
ለአንተ ጌታ አያቅትህም
ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ