Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የተስፋ ቃሉን

Yetesfa Qalun

1998 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንደተናገረን አደረገው

አወራለሁ እኔ ባይኖቸ ስላየሁ

ዘምራለሁ እኔ እመሰክራለሁ (፪x)

ልዩ ነው ድንቅ ነው

ምሥጋናችን ይሄው

ልዩ ነው ድንቅ ነው

ለኛ ያደረገው

፩) ተረስተናል እኛ አንቅም ብለን

ጉድጓድ ለኛ ጠልቋል ስንል አበቃልን

የተስፋ ቃል ኪዳን የሰጠን እግዚአብሔር

ባይናችን አየነው ሲያወጣን በክብር (፪x)

እንደተናገረን አደረገው

አወራለሁ እኔ ባይኖቸ ስላየሁ

ዘምራለሁ እኔ እመሰክራለሁ (፪x)

ልዩ ነው ድንቅ ነው

ምሥጋናችን ይሄው

ልዩ ነው ድንቅ ነው

ለኛ ያደረገው

፪) ጠላት በሩጫችን ፍላጻን ወርውሮ

ያሰብነውን ስናይ ሊያስቀረን ሞክሮ

በሳት በደመና የታደገን ጌታ

ፍላጻን ሰበረ ሆነልን መከታ (፪x)

እንደተናገረን አደረገው

አወራለሁ እኔ ባይኖቸ ስላየሁ

ዘምራለሁ እኔ እመሰክራለሁ (፪x)

ልዩ ነው ድንቅ ነው

ምሥጋናችን ይሄው

ልዩ ነው ድንቅ ነው

ለኛ ያደረገው

፫) አይችልም አትበሉ እግዚአብሔር ይችላል

ኤልሻዳይነቱን ታሪክ ይናገራል

ባሳለፍነው ጊዜ እኛም አይተነዋል

ያለውን አድራጊ ጌታ ነው ብለናል (፪x)

የተስፋ ቃሉን ፈጸመው

እንደተናገረን አደረገው

አወራለሁ እኔ ባይኖቸ ስላየሁ

ዘምራለሁ እኔ እመሰክራለሁ (፪x)

ልዩ ነው ድንቅ ነው

ምሥጋናችን ይሄው

ልዩ ነው ድንቅ ነው

ለኛ ያደረገው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ