የበግን መንጋ
Yebegen Menga
1998 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የበግ መንጋ ስጠብቅ
ስሙን በዜማ ሳደንቅ
ልዑል አየና ከሰማይ
ልቡ አረፈ በእኔ ላይ
አዝማች · Chorus
እንዴት ያለ ዓይን አለው (፪x)
ከሰው ልጆች ልዩ ነው
ሃሌሉያ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ደካማነቴንም አውቆ
አንበሳውን ለእኔ ለቆ
ጠላቴ ብዙ ሲሞክር
መጋጋውን ሰባብሮ
አዝማች · Chorus
የረዳኝ እግዚአብሔር ነው (፪x)
በዝማሬ ላመስግነው
ሃሌሉያ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሀይልንም የሚያስታጥቀኝ
መንገዴንም የሚያቀና
አጽንቶ የሚያቆመኝ
ጠላቴንም የሚረታ
በአማላክት መካከል
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው
ክብሬ ትዘምርለት
ማዳኑ ለልጅ ልጅ ነው
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በሥጋ ታናሽ ብመስልም
ጐልያድ በእኔ ቢስቅም
የታመንኩበት ጌታ ነው
በጠጠር የሚዘረጋው
እኩያ አቻ የሌለው
አዝማች · Chorus
ብርቱ አምላክ እግዚአብሔር ነው (፪x)
ሃሌሉያ (፫x)
ተመስገን (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ