እግዚአብሔር ጸሎትን ይሰማል
Egziabhier Tseloten Yesemal
2011 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ
ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ
ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ
እንዲሁም በምድር ትሁን
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን
እናም የበደሉልን ይቅር እንደምንል
በደላችንን ይቅር በለን
ከክፉ አድነን እንጂ ወደፈተናም አታግባን
መንግሥት የአንተ ናትና
ሃይልም ክብርም ለዘለዓለም አሜን (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ጸሎትን ይሰማል (፬x)
ኦ ጌታ ጸሎትን ይሰማል
ኦ ኢየሱስ ሰምቶ ይመልሳል
ቁጥር 2 · Verse 2
ሃናም ስትጸልይ ሰምቷታል
ልጅን ሰጥቷታል
እኛም ስንጸልይ ሰምቶናል
ድንቅ አድርጐልናል
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ጸሎትን ይሰማል (፬x)
ኦ ጌታ ጸሎትን ይሰማል
ኦ ኢየሱስ ሰምቶ ይመልሳል
ቁጥር 3 · Verse 3
ኤልያስ ሲጸልይ ሰቶታል
ሰማይ ተዘግቷል ደግሞም ተከፍቷል
እናንተም ጸልዩ ይሰማል
ድንቅን ያደርጋል
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ጸሎትን ይሰማል (፬x)
ኦ ጌታ ጸሎትን ይሰማል
ኦ ኢየሱስ ሰምቶ ይመልሳል
ቁጥር 4 · Verse 4
አባዬም ሲጸልይ ሰምቶታል መልሶለታል
እማዬም ስትጸልይ ሰምቷታል መልሶላታል
እናንተም ጸልዩ ይሰማል
ድንቅን ያደርጋል
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ጸሎትን ይሰማል (፬x)
ኦ ጌታ ጸሎትን ይሰማል
ኦ ኢየሱስ ሰምቶ ይመልሳል
ቁጥር 5 · Verse 5
ኦ ጌታ ጸሎትን ይሰማል
ኦ ኢየሱስ ሰምቶ ይመልሳል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ