Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እጅግ ደስ ይለዋል

Ejeg Des Yelewal

1999 · ትራክ 4 · 6:28 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምላኬ/ወዳጄ ሆይ በአንተ እጅግ ደስ ይለኛል

ወደር የለው ምህረትህ ፊትህ አቁሞኛል

ሁልጊዜ ማለዳ አዲስ ነህ ፍቅርህ አቻ የሌለው

ቸርነትህ በዛልኝ ሥምህን ላመስግነው (፪x)

ምህረትህ አቁሞኛል ሁልጊዜ ደስ ይለኛል

በልቤ ላመስግንህ ፈቅጄም ልገዛልህ (፪x)

ያስፈነድቀኛል ምህረቱ በዝቶ

ዘምር ያሰኘኛል ቸርነቱ በዝቶ

አመስግነው ይለኛል ደስ ደስም ይለኛል

አመስግን ይለኛል አሃ አሃ (፪x)

አምላኬ/ወዳጄ ሆይ በአንተ እጅግ ደስ ይለኛል

ወደር የለው ምህረትህ ፊትህ አቁሞኛል

ሁልጊዜ ማለዳ አዲስ ነህ ፍቅርህ አቻ የሌለው

ቸርነትህ በዛልኝ ሥምህን ላመስግነው (፪x)

ምህረትህ አቁሞኛል ሁልጊዜ ደስ ይለኛል

በልቤ ላመስግንህ ፈቅጄም ልገዛልህ (፪x)

አንደበቴን ልክፈት ጌታን ላመስግነው

ያዳነኝን አምላክ ከፍ ከፍ ላርገው

መንፈሱ ሲነካካኝ የሥጋዬን አስረሳኝ

ዘምር ዘምር አለኝ አሃ አሃ (፪x)

አምላኬ/ወዳጄ ሆይ በአንተ እጅግ ደስ ይለኛል

ወደር የለው ምህረትህ ፊትህ አቁሞኛል

ሁልጊዜ ማለዳ አዲስ ነህ ፍቅርህ አቻ የሌለው

ቸርነትህ በዛልኝ ሥምህን ላመስግነው (፪x)

ምህረትህ አቁሞኛል ሁልጊዜ ደስ ይለኛል

በልቤ ላመስግንህ ፈቅጄም ልገዛልህ (፪x)

ደስታዬ በአንተ ነው ሰላም ሆነኸኛል

ከማንም ከምንም አንተ አርክተኸኛል

ምህረትህ ቸርነትህ ሁሌ ይከተሉኛል

ፍቅርህ በዝቶልኛል አሃ አሃ (፪x)

አምላኬ/ወዳጄ ሆይ በአንተ እጅግ ደስ ይለኛል

ወደር የለው ምህረትህ ፊትህ አቁሞኛል

ሁልጊዜ ማለዳ አዲስ ነህ ፍቅርህ አቻ የሌለው

ቸርነትህ በዛልኝ ሥምህን ላመስግነው (፪x)

ምህረትህ አቁሞኛል ሁልጊዜ ደስ ይለኛል

በልቤ ላመስግንህ ፈቅጄም ልገዛልህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ