የልብ ወዳጅ
Yeleb Wedaj
1999 · ትራክ 2 · 6:02 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከእናቴም ከአባቴም ይልቅ የሚጠጋጋኝ ዘመዴ
ኢየሱስ ነው መከታ ለእኔ አፍቃሪ የልብ ወዳጄ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ፍቅሩን ሳስብ ይደንቀኛል ለእኔ ያሳየው ምህረቱ
ባወራው ባወራው አያልቅ ችሎኝ አለሁ በቤቱ
ትዕግሥቱ እጅግ ብዙ ነው አይሰለችም ይሸከማል
መልካም የበጐች እረኛ እንደ እርሱ ከየት ይገኛል
አዝማች · Chorus
ከእናቴም ከአባቴም ይልቅ የሚጠጋጋኝ ዘመዴ
ኢየሱስ ነው መከታ ለእኔ አፍቃሪ የልብ ወዳጄ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ውድ ነው ለእኔ ጌታዬ ዕንቁና ወርቅን ያስንቃል
ጠረኑ ከሩቅ የሚስብ መዓዛውም ደስ ያሰኛል
ፍቅር አለው ልብ የሚያረካ ወዳጄ ወረት አያውቅም
ነፍሱን ስለ እኔ ለውጧል ፍቅሩን በሞት ገልጾልኛል
አዝማች · Chorus
ከእናቴም ከአባቴም ይልቅ የሚጠጋጋኝ ዘመዴ
ኢየሱስ ነው መከታ ለእኔ አፍቃሪ የልብ ወዳጄ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ታማኝ ነው የማይለወጥ ጓደኛ ጊዜ አይቶ የማይርቅ
የዘለዓለም ሕይወት ዋሴ ኢየሱስ አዳኝ ለነፍሴ
ድቅድቅ ጨለማን የሚገፍ ብርሃን ይሁን ይብራ ያለ
ድንቁ የሰላም አለቃ ኧረ እንደ ጌታ ማን አለ
አዝማች · Chorus
ከእናቴም ከአባቴም ይልቅ የሚጠጋጋኝ ዘመዴ
ኢየሱስ ነው መከታ ለእኔ አፍቃሪ የልብ ወዳጄ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ