አለቴ ነው
Aletie New
1999 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምሕረቱ ገንኖ በእኔ ላይ መልካም የሆነውን ቀን እንዳይ
ጨለማዬን ሁሉ አብርቶአል ሃዘን ትካዜም ከእኔ ርቋል
አንደበቴን ልክፈት ልናገር ያደረገልኝን ድንቅ ነገር
መልካምነቱ ህሉ ይሰማ በእርሱ ዘንድ ዓይኖርም ጨለማ
አዝማች · Chorus
እርሱ የእኔ ወዳጅ እርሱ የእኔ እረኛ (፪)
ለምን እሰጋለሁ ለምን ልቤ ይፍራ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዓለቴ ነው ጌታዬ ጽኑ ነው መሠረቴ
እኔ ክፉን አልፈራም ኢየሱስ አለ በሕይወቴ
ሃላፊው እርሱ ነው በእኔ ላይ ልረፍ እንጂ እኔ ምን አሰጋኝ?
ብጨነቅ ባወጣው ባወርደው አንድም የለም የምጨምረው
ታማኝ ነው የእኔ እረኛ የማይደክም ከቶ የማይተኛ
ሃሣቤን በእርሱ ላይ እጥላለሁ ይረዳኛል አምኜዋለሁ
አዝማች · Chorus
በቸርነቱ እጄን ይዞ ትላንትናን እንዳሳለፈኝ
ለዛሬውም አምላኬ አለልኝ ለምን ልፍራ ምን አስጨነቀኝ?
ቁጥር 3 · Verse 3
ምሕረቱና ቸርነቱ ሁልጊዜ ይከተሉኛል
አይተወኝም ለዘለዓለም ኢየሱሴ ቃል ገብቶልኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ