የተገለጠው እውነት
Yetegeletew Ewnet
1999 · ትራክ 1 · 5:28 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንደበትህ ዝም አይበል አመስግን ይለኛል
የተገለጠው እውነት መቼ ዝም ያሰኛል
ክንፍ አውጥቼ እንደ ንስር እንድወጣ አድርጐኛል
የደከመ ጉልበቴን ጌታ አድሶልኛል
ጌታ ነዉ (፪x)
ጌታ ነዉ ኢየሱሴ ጌታ ነዉ
ኃያል ነዉ (፪x)
ኃያል ነዉ ጌታዬ ኃያል ነዉ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፍቅሩ ተገልጧል ደግነቱ
ተስፋ ለቆረጡ ማጽናናቱ
አቤት ምሕረቱ (፬x)
ምህረቱ አጽንቶ አቁሞኛል
በኢየሱሴ ብርሃን ወጥቶልኛል
ዘምራለሁ ንጉሤን አከብራለሁ
የእርሱን ማዳን ለልጅ ልጅ አወራለሁ
አዝማች · Chorus
አንደበትህ ዝም አይበል አመስግን ይለኛል
የተገለጠው እውነት መቼ ዝም ያሰኛል
ክንፍ አውጥቼ እንደ ንስር እንድወጣ አድርጐኛል
የደከመ ጉልበቴን ጌታ አድሶልኛል
ጌታ ነዉ (፪x)
ጌታ ነዉ ኢየሱሴ ጌታ ነዉ
ኃያል ነዉ (፪x)
ኃያል ነዉ ጌታዬ ኃያል ነዉ
ቁጥር 2 · Verse 2
አፌን በዝማሬ እከፍታለሁ
የጌታዬን ክብር አወራለሁ
ንጉሥ እለዋለሁ (፬x)
እግዚአብሔር ነው ዘለዓለም ድንቅ ጌታ
ይገባዋል ምሥጋና በዕልልታ
ኦ! አክብሪው ነፍሴ ለእርሱ ተገዢ
ዛሬም ነገም ኢየሱስ ነው ተስፋሽ
አዝማች · Chorus
አንደበትህ ዝም አይበል አመስግን ይለኛል
የተገለጠው እውነት መቼ ዝም ያሰኛል
ክንፍ አውጥቼ እንደ ንስር እንድወጣ አድርጐኛል
የደከመ ጉልበቴን ጌታ አድሶልኛል
ጌታ ነዉ (፪x)
ጌታ ነዉ ኢየሱሴ ጌታ ነዉ
ኃያል ነዉ (፪x)
ኃያል ነዉ ጌታዬ ኃያል ነዉ
ቁጥር 3 · Verse 3
ዝማሬ መልካም ነው ኦ! ምሥጋና
ደግሜ ልባርከው ቸር ነውና
ዛሬም እንደገና (፬x)
ኦ! ጌታዬን ሁልጊዜ አመልከዋለሁ
ዘወትር ፊቱ ምሥጋናን እሰዋለሁ
አልሰለችም በጌታ ደስ ይለኛል
መንፈስ ቅዱስ ብርታትና ኃይል ሆኖኛል
አዝማች · Chorus
አንደበትህ ዝም አይበል አመስግን ይለኛል
የተገለጠው እውነት መቼ ዝም ያሰኛል
ክንፍ አውጥቼ እንደ ንስር እንድወጣ አድርጐኛል
የደከመ ጉልበቴን ጌታ አድሶልኛል
ጌታ ነዉ (፪x)
ጌታ ነዉ ኢየሱሴ ጌታ ነዉ
ኃያል ነዉ (፪x)
ኃያል ነዉ ጌታዬ ኃያል ነዉ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ