Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምላኬ ነህ

Amlakie Neh

1999 · ትራክ 11 · 5:04 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እኔማ ምን ልበል ስንቱን አወራለሁ

የቱንስ አውርቼ የቱን እተዋለሁ

ያደረገልኝን ብቆጥር በየተራ

ከአዕምሮዬ በላይ ሆነ የእርሱ ሥራ

እኔማ ምን ልበል ስንቱን ላውራ

ከአዕምሮዬ በላይ ነው የእርሱ ሥራ (፪x)

ክብር የእግዚአብሔር ነው

ክብር የኢየሱስ ነው (፪x)

ተመስገን የምለው ካሳ ሆኖ አይደለም

የጌታን ውለታ የሚክሰው የለም

ክበርም የምለው ስለሚገባው ነው

ለውለታው ምላሽ ሊሰጥ የሚችል ማነው

እኔማ ምን ልበል ስንቱን ላውራ

ከአዕምሮዬ በላይ ነው የእርሱ ሥራ (፪x)

አምላኬ ነህ ጌታዬ/ኢየሱሴ ወዳጄ እንከን የሌለህ

ፍቅርህ ለእኔ በቂ ነው ሁሌ ታጠግበኛለህ (፪x)

ስለዚህ (፪x) በፍፁም ልቤ ጌታዬ ወድሃለሁ

ዘመኔን (፪x) እያከበርኩህ ለመኖር ወስኛለሁ (፪x)

ከእርሱ የሆነውን ለእርሱ አቀርባለሁ

እኔማ ምን አለኝ ምን እሰጠዋለሁ

እንዲሁ በፀጋው ፊቱ አቁሞኛል

ስለፈቀደልኝ አመስግን ብሎኛል

ስለፈቀደልኝ አሃሃ አመስግን ብሎኛል አሃሃ

ስለፈቀደልኝ ኦሆሆ አክብረኛል ብሎኛል አሃሃ

አምላኬ ነህ ጌታዬ/ኢየሱሴ ወዳጄ እንከን የሌለህ

ፍቅርህ ለእኔ በቂ ነው ሁሌ ታጠግበኛለህ (፪x)

ስለዚህ (፪x) በፍፁም ልቤ ጌታዬ ወድሃለሁ

ዘመኔን (፪x) እያከበርኩህ ለመኖር ወስኛለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ