Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሁሉን እንደዋዛ

Hulun Endewaza

1999 · ትራክ 6 · 5:01 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታ ነው በሕይወቴ መልካም ያደረገው

እርሱ ነው በሕይወቴ ድንቅን ያደረገው

አምላኬ ነው በእኔ በላይ መልካም ያደረገው

እርሱ ነው በሕይወቴ ድንቅን ያደረገው

ይገርመኛል ይደንቀኛል

ኦ ጌታዬ ሥራው ይገርመኛል (፪x)

አምላኬ ባይርዳኝ እጄን ይዞ

እንዴት ይታለፋል ጠላቴ መንገድ ዘግቶ

ኦ ምሕረቱ ለእኔ ስለበዛ አሃ

አሳለፈኝ ጌታ ሁሉን እንደዋዛ (፪x)

ጌታ ነው በሕይወቴ መልካም ያደረገው

እርሱ ነው በሕይወቴ ድንቅን ያደረገው

አምላኬ ነው በእኔ በላይ መልካም ያደረገው

እርሱ ነው በሕይወቴ ድንቅን ያደረገው

ይገርመኛል ይደንቀኛል

ኦ ጌታዬ ሥራው ይገርመኛል (፪x)

ዓይኖቼን ከፈተ ጌታ ገለጠልኝ

የሰማዩን መልካም ነገር አበራልኝ

ኦ ደስ ይለኛል በእርሱ ለዘለዓለም አሃ

አመልካለሁ ጌታን ኧረ እንደ እርሱ የለም (፪x)

ጌታ ነው በሕይወቴ መልካም ያደረገው

እርሱ ነው በሕይወቴ ድንቅን ያደረገው

አምላኬ ነው በእኔ በላይ መልካም ያደረገው

እርሱ ነው በሕይወቴ ድንቅን ያደረገው

ይገርመኛል ይደንቀኛል

ኦ ጌታዬ ሥራው ይገርመኛል (፪x)

በዕረፍት ውኃ ዘንድ እኔን የሚመራኝ

በጠላቶቼ ፊት ዘይትን የቀባኝ

ጽዋዬን ሞላው ጌታ አትረፈረፈኝ አሃ

በመንገዴ ላይ እርሱ ምርኩዜ ሆነልኝ (፪)

ሃሌሉ ሃሌሉያ (፫x)

ሃሌ ሃሌ ሃሌሉያ (፫x)

ጌታ ነው በሕይወቴ መልካም ያደረገው

እርሱ ነው በሕይወቴ ድንቅን ያደረገው

አምላኬ ነው በእኔ በላይ መልካም ያደረገው

እርሱ ነው በሕይወቴ ድንቅን ያደረገው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ