ሰላም
Selam
1999 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሰላም ነው ከጌታ ጋር ውሎ ማደር
መልካም አምላክ በእቅፉ ይዞኛል
አልሻም ምንም ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለም
ፍቅሩ ከጨለማ ስቦ አውጥቶኛል
ሁሉን በሚችለው አምላክ ጥላ ስር አድራለሁ
ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ
ጌታ መልካም አምላክ ነው (ኦሆሆሆ)
ጌታ መልካም አምላክ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰላምን ይሿታል በወርቅ በብር ሊያገኟት
በዓልማዝ በዕንቁ አትመጣም ምን ያህል ቢያፈሱላት
ከእግዚአብሔር የታረቀ እርሱ ነው የዘየደ
በአምላክ ሰላም ይጠግባል በመንገዱ የሄደ (፪x)
በፈቃዱ የሄደ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሰላም ነው ከጌታ ጋር ውሎ ማደር
መልካም አምላክ በእቅፉ ይዞኛል
አልሻም ምንም ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለም
ፍቅሩ ከጨለማ ስቦ አውጥቶኛል
ሁሉን በሚችለው አምላክ ጥላ ስር አድራለሁ
ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ
ጌታ መልካም አምላክ ነው (ኦሆሆሆ)
ጌታ መልካም አምላክ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሆድ በእንጀራ ቢሞላ ገላም ምርጡን ቢለብስ
የነፍስ ጐዶሎ አይሞላም ሰው ሁሉን ቢያግበሰብስ
ሰማያዊው ደስታ አምላክ ከላይ የላከው
ሰላም ማለት ኢየሱስ ነው ተሰፍሮ የማይለካው (፪x)
ሰው ዓለምን አትርፎ ውድ ነፍሱን ቢያዶላት
ከቶ ምን ይጠቅመዋል መጨረሻው ነው ጥፋት
ብሩክ ትሁን ያቺ ቀን ወንጌል የሰማሁባት
በክርስቶስ መስቀል ስራ ከአምላክ ጋር የታረቅኩባት (፪x)
ወንጌል የሰማሁባት አሄ ሰላም ያገኘሁባት
አዝማች · Chorus
ሰላም ነው ከጌታ ጋር ውሎ ማደር
መልካም አምላክ በእቅፉ ይዞኛል
አልሻም ምንም ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለም
ፍቅሩ ከጨለማ ስቦ አውጥቶኛል
ሁሉን በሚችለው አምላክ ጥላ ስር አድራለሁ
ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ
ጌታ መልካም አምላክ ነው (ኦሆሆሆ)
ጌታ መልካም አምላክ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ