Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኦ ፍቅሩ

O Feqru

1999 · ትራክ 10 · 4:21 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኦ ፍቅሩ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል

ሁልጊዜ ያስገርመኛል

ምሕረቱ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል

ሁልጊዜ ያስገርመኛል

የድሃ አደግ ወዳጅ የምስኪን ጓደኛ

ማን እንደ ኢየሱሴ ታማኝ ሚስጥረኛ

መድኃኒቴ እርሱ ነው ሁሌ አመልከዋለሁ

ምሥጋናም ክብርም ዝማሬም ለእርሱ ነው (፮x)

ኦ ፍቅሩ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል

ሁልጊዜ ያስገርመኛል

ምሕረቱ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል

ሁልጊዜ ያስገርመኛል

ኃጥያተኛ ብሎ ሁሉም ተፀይፏት

ያለርህራሄ በድንጋይ ሊወግሯት

እንዳትሞት የሚፈልግ ተገኘ የሚወዳት

ጥበብን ተናግሮ ከጨካኙ አዳናት

አትሞቺም አላት(፭x)

ኦ ፍቅሩ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል

ሁልጊዜ ያስገርመኛል

ምሕረቱ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል

ሁልጊዜ ያስገርመኛል

የአንዲቷ ነፍስ ጌታን በጣም ግድ ብሎት

በሰማሪያ መንገድ አለፈ ሊያድናት

የነፍሷን ጥያቄ የውስጧን ፈታላት

የሕይወትን ውኃ አፍለቀለቀላት

አትጠሚም አላት(፭x)

ኦ ፍቅሩ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል

ሁልጊዜ ያስገርመኛል

ምሕረቱ ሁልጊዜ ያስደንቀኛል

ሁልጊዜ ያስገርመኛል

አቤቱ ጌታዬ ሁሌ አከብርሃለሁ

ፍቅርህን እያሰብኩ እገዛልሃለሁ

ምሥጋና ይገባሃል ንገሥ ለዘለዓለም

በሰማይ በምድር ኧረ እንዳንተ የለም (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ