እንዴት እፈራለሁ
Endiet Eferalehu
2008 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ተጨንቃ ለነበረች ነፍሴ ጨለማን አይሆንም ሲል
አዋጅን በአዋጅ ሽሮ መርዶዬን ሲከለክል
ከፊቴ ቀድሞ ሲወጣ ተራራን ሲደለድል
ሥራዬን ሰርቶ ሲጨርስ ችግሬን ሲጠቀልል
መቃብሬን ሲከፍተው ታምር ሲሰራ
ነፍሴን እጅግ ሲያስጨንቅ በእኔ ሲፈራ
ታምራት ሲያስለምደኝ ሲያሳየኝ ኖሬ
እንዴት እሸበራለሁ እፈራለሁ ዛሬ
አዝማች · Chorus
እንዴት እንዴት እፈራለሁ (፫x)
ለምን ለምን እሰጋለሁ (፫x)
የተሸከመኝ ትልቅ አምላክ ነው (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስንቱን ሸለቆ ስንቱን ተራራ
ጥሼ ሄጃለሁ ከእርሱ ጋራ (፪x)
እያሪኮዬ ቅጥሩ ሲፈርስ
አይታለች ነፍሴ በኢየሱስ (፪x)
ስለዚህ አልፈራም ምድር ብትናወጥ
በዙፋኑ እያለ ከቶ ከቶ ማይናወጥ (፪x)
በዙፋኑ እያለ ከቶ ከቶ ማይናወጥ (፪x)
አዝማች · Chorus
እንዴት እንዴት እፈራለሁ (፫x)
ለምን ለምን እሰጋለሁ (፫x)
የተሸከመኝ ትልቅ አምላክ ነው (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በእሳት ማሃል መንገድ ያለው ጌታ
መቼ ትቶኝ ያውቃል አንድ አፍታ
ማዕበልና ወጀቡን አራምዶ
ያሻግረኛል ከባህር ማዶ
ስለዚህ አልፈራም ምድር ብትናወጥ
በዙፋኑ እያለ ከቶ ከቶ ማይናወጥ (፪x)
በዙፋኑ እያለ ከቶ ከቶ የማይናወጥ (፪x)
አዝማች · Chorus
እንዴት እንዴት እፈራለሁ (፫x)
ለምን ለምን እሰጋለሁ (፫x)
የተሸከመኝ ትልቅ አምላክ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ