እግዚአብሔር መልካም ለእኔ
Egziabhier Melkam Lenie
2008 · ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ
እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በወይን ሐረግ ዘንድ ፍሬ ባይገኝ
ባይኖር የሚረዳ ከግራ ከቀኝ
በለሷን ጠብቄ ፍሬን እበላለሁ
ቀኝ እጄን የያዘኝ መቼ ሊረሳኝ ነው
እሱን ታምኖ ጠርቶ ከቶ ማንስ አፍሯል
ይልቁን በስሙ ቀንዱ ከፍ ብሏል
እኔም በስሮቼ ከፍ ከፍ እላለሁ
አለኝ የሚረዳ ይህንን አውቃለሁ (፫x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ
እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጨለማው በርትቶ ማይነጋ ሲመስል
ዮርዳኖስም ሞልቶ አላሻግርም ሲል
ታምራት አድርጎ ያሻገረው ጌታ
እግዚአብሔር መልካም ነው ዛሬም በእኔ ቦታ
ሞትን ያሸነፈ ድል የነሳ ጌታ
ሰባቱን ማህተም ተርትሮ የፈታ
ዛሬም በቸርነት ይከታተለኛል
እሱን ተደግፌ ምንስ ያሰጋኛል (፫x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ
እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወረት የለበትም ፍቅሩ ሁሌ ስያፈቅር ይኖራል
መንገድ አስጀምሮ ጉዞ መች እዚህ አውጥቶ ይሄዳል
እቅፍ ድግፍ አርጎ ይዞ በብዙ ሞገስ ያኖራል
ላይተው ላይረሳ በራሱ በስሙ ኪዳን ይምላል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ