ዘመን መጣ
Zemen Meta
2008 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሞቴን በሕይወት ቀይሮ ነገሬን ሊገለብጥ
በጭንቀቴ ሊያሰፋ ከፍታን ለእኔ ሊሰጥ
አዎ ዘመን መጣ ከፊቴ ፋሬስ ብዬ የምጥስበት
የያዘኝ ዳግም ላይዘኝ ሰብሬ የምወጣበት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰባሪው ጌታ ከፊቴ ወጥቷል
አማሌቅ ፈርቶ መንገዴን ለቋል
ክረምቱ አልፎ ጭጋጉ በኗል
ዛሬ ለእኔ የዜማ ጊዜዬ ሆኗል
አዝማች · Chorus
አምልኮ ይዤ ልምጣ እኔም በተራዬ (በተራዬ) (፪x)
ሌሊቱን በሚያነጋው ታብሷል እምባዬ (ታብሷል) (፪x)
አምልኮ ይዤ ልምጣ (ይዤ ልምጣ) እኔም በተራዬ (፪x)
ቀን ቀጥሮ በሚመጣው (በሚያነጋው) ታብሷል እምባዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከአለት ንቃቃት የምወጣበት እጄን በአፌ ላይ የምጭንበት
የጠላቴ አፍ የሚዘጋበት ዘመን መጣ የምከብርበት
ከእንግዲህ በቃ ማልቀስ በሸለቆ የናሱም ደጃፍ ተበርግዷል አውቆ
ልሂድ ልውረሰው ከቶ አታዘግዩኝ እግዚአብሔር ነው ውረሺው ያለኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔር ነው ውረሺው ያለኝ (፬x)
በቃ ሌሊቱ ነጋ በጠላቴ ላይ ተዘጋ
ጌታ ቀኝ እጄን ይዞ አሻገረን ከእርሱ ጋር
ማንኮራኩሩ ታስሮ ተጨነቀ ጠላቴ
እኔ ግን እየዘመርኩ ገባሁኝ ወደርስቴ
የማንም እምባ ባለዕዳ አይደለም ጌታ
ዘመናት ቆጥሮ ያቆማል በከፍታ (፪x)
ከፍ ይበል ጌታ ማህተሜን የፈታ (፬x)
አዝማች · Chorus
አምልኮ ይዤ ልምጣ እኔም በተራዬ (በተራዬ) (፪x)
ሌሊቱን በሚያነጋው ታብሷል እምባዬ (ታብሷል) (፪x)
አምልኮ ይዤ ልምጣ (ይዤ ልምጣ) እኔም በተራዬ (፪x)
ቀን ቀጥሮ በሚመጣው (በሚያነጋው) ታብሷል እምባዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ