Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መዳኔ ይገርመኛል

Medanie Yigermegnal

2008 · ትራክ 3 · 5:52 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

መዳኔ ይገርመኛል (፫x)

ታምር ያሰኘኛል (፪x)

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ሲዖል ሲዘጋ

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ለእኔ ሲነጋ

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ከእስር ስፈታ

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ጠላት ሲመታ (፪x)

ጠላት ሲመታ (፰x)

ጨለማው ሲገፈፍ ብርሃን ሲበራ (፪x)

አልቆ ተፈጽሞ ነገሬ ሲሰራ (፪x)

በዚያ የመስቀል ደም ሰላም ሲደረግ (፪x)

እዳዬን ስከፍለው የእግዚአብሔር በግ (፪x)

እግዚአብሔር ሲዋጋ (፫x)

ዘንዶ ተገደለ ጠላቴ ተወጋ

ነገር ተገልብጦ እኔ ሰፈር ነጋ (፪x)

መዳኔ ይገርመኛል (፫x)

ታምር ያሰኘኛል (፪x)

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ሲኦል ሲዘጋ

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ለእኔ ሲነጋ

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ከእስር ስፈታ

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ጠላት ሲመታ (፪x)

ጠላት ሲመታ (፰x)

አትሞቺም ብሎ ሞቴን ገደለና (፪x)

በሕይወት አኖረኝ ኪዳኑን አጸና (፪x)

ያ ባለጋራዬም ዕቅዱ ፈረሰ (፪x)

እግዚአብሔር በኢየሱስ ዕንባዬን አበሰ (፪x)

እግዚአብሔር ተነሳ (፫x)

መከራዬን ወስዶ ሀዘኔን አስረሳ

መታሰቢያ አረገ ሥሙን እንዳልረሳ (፪x)

መዳኔ ይገርመኛል (፫x)

ታምር ያሰኘኛል (፪x)

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ሲኦል ሲዘጋ

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ለእኔ ሲነጋ

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ከእስር ስፈታ

ከዚህ በላይ ታምር ምንድን ነው ጠላት ሲመታ (፪x)

ጠላት ሲመታ (፰x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ