ቀንበር ሰብሮ
Qenber Sebro
2008 · ትራክ 11 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቀንበር ሰብሮ እስራትን የሚፈታ
አሃሃሃ ማን እንደ ጌታ ማን እንደኢየሱስ ማን እንደጌታ
ከፍ የሚያደርግ አንስቶ ከውርደት ቦታ
አሃሃሃ ማን እንደጌታ ማን እንደ ኢየሱስ ማን እንደጌታ
ለዚህ ጌታ እሰግድለታለሁ
ተሸክሞኝ እዚህ ደርሻለሁ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለዚህ ንጉሥ እቀኝለታለሁ
በእርሱ ብርታት ዛሬን አይቻለሁ
ምስኪን ችግረኛን እንደማንም ሳይተው
እንደ ባለማዕረግ ስፍራን የሚሰጠው
የወደቀን ማንሳት ክብር የሆነለት
መታሰቢያም ሚያቆም ሰርቶ ታምራት
ባርኮ እየባረከ በእርሱ ደግነት
አክብሮ የሚያኖር ነው መልካም አባት (፪x)
አዝማች · Chorus
ቀንበር ሰብሮ እስራትን የሚፈታ
አሃሃሃ ማን እንደ ጌታ ማን እንደኢየሱስ ማን እንደጌታ
ከፍ የሚያደርግ አንስቶ ከውርደት ቦታ
አሃሃሃ ማን እንደጌታ ማን እንደ ኢየሱስ ማን እንደጌታ
ለዚህ ጌታ እሰግድለታለሁ
ተሸክሞኝ እዚህ ደርሻለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ለዚህ ንጉስ እቀኝለታለሁ
በእርሱ ብርታት ዛሬን አይቻለሁ
ምሕረቱን አብዝቶ ሞገስ የሚሰጥ
የጠላትን ከፍታ ወስዶ ሚያስረግጥ
በክንፎቹ ጥላ ሸሽጎ የሚያኖር
ተማምኖ ለተራው ስሙን የሚያከብር
እጅግ የሚራራ የበዛ እርዳታው
እንደ እግዚአብሔር ያለ ደግ አምላክ ማን ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ቀንበር ሰብሮ እስራትን የሚፈታ
አሃሃሃ ማን እንደ ጌታ ማን እንደ ኢየሱስ ማን እንደጌታ
ከፍ የሚያደርግ አንስቶ ከውርደት ቦታ
አሃሃሃ ማን እንደጌታ ማን እንደ ኢየሱስ ማን እንደጌታ
ለዚህ ጌታ እሰግድለታለሁ
ተሸክሞኝ እዚህ ደርሻለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ለዚህ ንጉስ እቀኝለታለሁ
በእርሱ ብርታት ዛሬን አይቻለሁ
ከፍ ከፍ ይበል የእኔ ጌታ ከፍ ከፍ ይበል
ከፍ ከፍ ይበል የእኔ ወዳጅ ከፍ ከፍ ይበል
እንደሱ ጌታ እስቲ የታል (፪x)
እንደሱ ፍቅር እስቲ የታል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ