እኔ የማምነው
Enie Yemamnew
2008 · ትራክ 6 · 6:43 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዙሪያዬ ያለው ነገሬ ይህን ባይነግሬኝ
ነገርሽ ሞተ ተቀበረ በቃ ብለኝ
አዲስ ነገር ማድረግ ሁልጊዜ ልማድ ያለው ጌታ
ዛሬም በዙፋኑ ይተጋል ስለ እኔ ከፍታ (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ የማምነው ጨለማሽ ይበራል ያለኝን ነው (፪x)
እኔ የማምነው ተራራሽ ይናዳል ያለኝን ነው (፪x)
አላምንም ሁኔታን አላምንም ችግሬን
እግዚአብሔርን አምነዋለሁ ይሰራል ነገሬን (፪x)
እግዚአብሔርን አምነዋለሁ ይከፍታል መቃብሬን (፪x)
ልቤን ልጣል እንጂ በሚያስጥለው ጌታ
በእርሱ ተደግፌ ጉልበቴን ላበርታ
ታምራት ያሳየኛል ጌታ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በደረቁ አጥንቶች ነፍስን መዝራት
እንደ ሰው ሲታሰብ በምን ጉልበት
እንደ እግዚአብሔር ግን ቀላል ነው
እጁ ድንቅ ይሰራል ትልቅ ነው
ልጅ መውለድ በዘጠና ዓመት
ለሣራ ከባድ ነው ሲገመት
ግን እግዚአብሔር ካለ ሆነ ነው
ታምር የሚሰራ ጌታ ነው [1]
እርሱ ትልቅ ነው እግዚአብሔር ከሁኔታ በላይ
ኧረ እርሱ ትልቅ ነው እግዚአብሔር ከሁኔታ በላይ
ያልታሰበ ነገር ያደርጋል በሞተው ነገር ላይ (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ የማምነው ጨለማሽ ይበራል ያለኝን ነው (፪x)
እኔ የማምነው ተራራሽ ይናዳል ያለኝን ነው (፪x)
አላምንም ሁኔታን አላምንም ችግሬን
እግዚአብሔርን አምነዋለሁ ይሰራል ነገሬን (፪x)
እግዚአብሔርን አምነዋለሁ ይከፍታል መቃብሬን (፪x)
ልቤን ልጣል እንጂ በሚያስጥለው ጌታ
በእርሱ ተደግፌ ጉልበቴን ላበርታ
ታምራት ያሳየኛል ጌታ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ