ኢትዮጵያ
Ethiopia
2003 · ትራክ 5 · 5:51 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢትዮጵያ ሃገሬ ኢትዮጵያ
መልካም እንዲሆንልሽ ዛሬ
ስሚልኝ ይህቺን ዝማሬ (፪x)
አምላክሽ እኮ ቀናተኛ ነው
ለሌላ አማልክት መስገድሽ ምነው
ለሱ ለአምላክሽ ብቻ ስገጂ
እጆችሽንም ወደእርሱ ዘርጊ
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ (፬x)
ኢትዮጵያ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እርሱ እኮ ላንቺ መፍትሔ አለው
የሚጠራሽ ሊያሳርፍሽ ነው
ነይ ወደሱ ሸክምሽ ከብዷል
ተጠጊው እርሱን ያሳርፍሻል
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ (፬x)
ኢትዮጵያ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሊገነባሽ ነው በአዲስ ድንጋይ
ተነስቷል ባንቺ ኤልሻዳይ
አንቺም ተነሺ ተቀበይው
አምላኬ እንተ ውዴ ነህ በይው
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ (፬x)
ኢትዮጵያ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ኢትዮጵያ ፈጥና እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች (አሜን)
ኢትዮጵያ ሃገሬ ኢትዮጵያ
መልካም እንዲሆንልሽ ዛሬ
ስሚልኝ ይህቺን ዝማሬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ