Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅር ከመቃብር በላይ

Feqer Kemeqaber Belay

2003 · ትራክ 6 · 5:04 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፍቅር እስከ መቃብር (፬x)

የስንቶች ፍቅር እስከ መቃብር

የኛ ግን ኢየሱስ የኛ ግን ኤልሻዳይ

የርሱ ፍቅር ያልፋል ከመቃብር በላይ

ፍቅር ያልፋል ከመቃብር (፬x)

ፍቅርን የተራበ ፍቅርን የተጠማ ከውስጡ ካንጀቱ

ስለፍቅር አይነት ቢሰማ አይሰለቸው ተርቧል ከእውነቱ

አውቋል አንድ ነገር የፍቅርን መቋጫ የመጨረሻውን

ከመቃብር ድረስ የገባውን ኪዳን ውሉን ማስረጃውን

ግን ደግሞ አለ ሌላ መቃብር ያለፈ ፍቅሩ ያልተሸነፈ

በፍቅር ተይዞ ያለምክንያት ወርዶ ከመቃብር ማዶ

ተቀብሮ ያልቀረ ጥሶ የተሻገረ ጭራሹን ያረገ

ሞቶ የተነሳ ሃዘን የሚያስረሳ የይሁዳ አንበሳ

በምድር ያለ ሁሉ ቢጠራ ቢጠራ ለችግረኛ ሰው ምኑ ነው የሚራራ

ሞትህ ለኔ ይሁን እያለ ሰው ውሸቱን በስራ ያሳየ አግኝተናል አንዱን

ከመቃብር በላይ ፍቅሩን የገለጠ ቢጠቀስ አንድ የለም ከጌታ የበለጠ

ከጌታ የበለጠ (፪x)

ፍቅር እስከ መቃብር (፬x)

የስንቶች ፍቅር እስከ መቃብር

የኛ ግን ኢየሱስ የኛ ግን ኤልሻዳይ

የርሱ ፍቅር ያልፋል ከመቃብር በላይ

ፍቅር ያልፋል ከመቃብር (፬x)

በቁሙ የተጠላ የተኮራረፈ የሚዘጋበት በር

የሞቱ ቀን ደግሞ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል አብሮ ለመቀበር

መውደዱን ሲገልጽ በእንጉርጉሮ ዜማ አልቃሽ አስጠርቶ

የአርባው እለት ደግሞ ሙሾ ሲያወጣለት ሐውልት አሰርቶ

አቤት ሲዋደዱ ይላል ደግሞ ሌላው ነገሩ ያልገባው

ይደነቃል ብሎ የነዚህስ ፍቅር ነው እስከ መቃብር

አልሰማ የኔን ነገር ወዶኝ ስለሞተ ነፍሱን ስለሰጠ

የኔ ብርቱ አፍቃሪ ከመቃብር በላይ ሄዷል ወደሰማይ

በፍቅር እስራት ገመድ የገመደ ከሰው ጋር ሊወዳጅ ከላይ የወረደ

አብሮ ሄዶ ሄዶ ጫፍ እየደረሰ አይሰናበትም እየተመለሰ

ምድርና ሞላዋን ቢገለባብጠው ይምጣና ይወራረድ ጌታዬን አይበልጠው

ጌታዬን አይበልጠው (፪x)

ፍቅር እስከ መቃብር (፬x)

የስንቶች ፍቅር እስከ መቃብር

የኛ ግን ኢየሱስ የኛ ግን ኤልሻዳይ

የርሱ ፍቅር ያልፋል ከመቃብር በላይ

ፍቅር ያልፋል ከመቃብር (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ