አላማዬ
Alamayie
2003 · ትራክ 4 · 5:42 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አላማዬ አይደለም እራስን ማስከበር
አላማዬ አይደለም ለታይታ መቅረብ
አላማዬ አይደለም ከፍ ብሎ መታየት
አላማዬ አይደለም በዓለም ታዋቂነት
አዝማች · Chorus
አላማዬ ለመኖር ነው አስከብሬው ኢየሱሴን
አላማዬ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዋሽቶም ሰርቆም መስሎም አጭበርብሮም ሊያሸንፈው ይታገላል ኑሮን
ለሕሊናው ክስ ያስተባብላል ይሞታል ወይ ብሎ ያሳብባል
የሰው ጭንቀት ለመኖር ብቻ ነው ስለነገ ማሰብ ለከንቱ ነው
ነገ ይጨነቅ ስለራሱ ብሎ አላማ አለኝ ከሁሉ አስበልጦ
አላማዬ የከንቱ አይደለም
አላማዬ ታይቶ የሚጠፋ
አላማዬ ስራ ፈት አይደለም
አላማዬ አለኝ ብዙ ስራ
አዝማች · Chorus
አላማዬ ለመኖር ነው አስከብሬው ኢየሱሴን
አላማዬ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አላማዬ አይደለም እራስን ማስከበር
አላማዬ አይደለም ለታይታ መቅረብ
አላማዬ አይደለም ከፍ ብሎ መታየት
አላማዬ አይደለም በዓለም ታዋቂነት
አዝማች · Chorus
አላማዬ ለመኖር ነው አስከብሬው ኢየሱሴን
አላማዬ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እልፍን በእጁ ይዞ ወደኋላ የሚያይን ሰው አልሆንም ተላላ
ከእንግዲህ ቀኝ ኋላ ዞሬ አልሄድም አላማዬን አውቃለሁ የያዝኩትን
ኢየሱሴ ሁን የሞቴ ማምለጫ ተገደብኩኝ ከከንቱ እሩጫ
ፍቅር የሆነው የርሱ አላማ ስለገባት ነፍሴም አታቅማማ
አላማዬ የከንቱ አየደለም
አላማዬ ታይቶ የሚጠፋ
አላማዬ ስራ ፈት አይደለም
አላማዬ አለኝ ብዙ ስራ
አዝማች · Chorus
አላማዬ ለመኖር ነው አስከብሬው ኢየሱሴን
አላማዬ (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
አላማዬ ለመኖር ነው አስከብሬው ኢየሱሴን
አላማዬ (፵x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ