የለወጠኝን
Yelewetegnen
2003 · ትራክ 7 · 4:48 · አማርኛ
እስኪ አክብሩልኝ የለወጠኝን (፪x)
አዲስ ስም ሰጥቶ የቀየረኝን (፪x)
ከማይጠፋው ዘር የወለደኝን (፪x)
ለቤቱ አገልጋይ ያደረገኝን (፪x)
እኔም ላክብረው ባለው ዘመኔ
ላዳነኝ ለርሱ ለዚህ መድህኔ
ብዘምርለት ሁሌ ብናገር
አይበዛበትም ላረገው ነገር
ስንቱን አውርቼ የቱን ልተው ውለታው በዝቷል (፪x)
የማዳኑን ክንድ በእኔ ለፍጥረት ገልጧል (፪x)
የእኔን መለወጥ ያየ ይበል አይበቃም (፪x)
ገና እጁ አላጠረም ያድናል ሌላም (፪x)
ክሩ በመርፌ የገባለት ሰው (፪x)
የዓይኑም እምባ ፈሶ የታበሰው (፪x)
በሩጫ ሜዳ መስመር ከያዘ (፪x)
ደካማው ሲወድቅ ብርቱው ካገዘ (፪x)
በመከናወን ማን ቅር ይሰኛል
አእምሮ ከሌለው ግን ቅር ይለዋል
ማሰብ የሚችል አእምሮው ጤነኛ
መከናወንን ይወዳልና
ታዲያ ምነው ቅር አላችሁ ስይዝ መስመሩን (፪x)
መከናወን ሲሆንልኝ ሲያወርሰኝ ክብሩን (፪x)
ከዚያ ካስጨናቂው አለም ሳመልጥ በርሬ (፪x)
ተከትሎኝ መምጣት እንጂ አይጠቅምም ወሬ (፪x)
ዕድሜዬን ሲጨምር ዓመት ሲበዛ (፪x)
ሲያሸጋግረኝ መስሎኝ የዋዛ (፪x)
ስቀልድባት በሕይወቴ ላይ (፪x)
መቼ አስቻለው ሲያየኝ ከሰማይ (፪x)
ለካ አስቀድሞ አስቦኝ ኖሯል
የመለወጤ ጊዜያቱ ደርሷል
እርሱ የመደበው ሰዓቱ አያልፍ
ጌታ ኢየሱሴን አግኝቼው ሳላርፍ
እኔም አላለፍኩ ከቀኑ ተማረኩለት (፪x)
የርሱ ፍቅር አይሎ እንጂ ምን አረግኩለት (፪x)
ምን አይቶብኝ ነው እንዳልል ራሱን አይቶ ነው (፪x)
ለውጦ ከቀያየረኝ ከልካዩስ ማነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ