ለሕይወትህ ዋጋ ስጥ
Lehiwoteh Waga Set
2003 · ትራክ 11 · 5:59 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የባህሪ ለውጥ አምጣ (፬x)
ከየት ይምጣ ከየት ይምጣ
ሰው ሁሉ ካለበት ሱስ ካልወጣ
ከየት ይምጣ ከየት ይምጣ
ሰው ሁሉ ደፍሮ እውነቱን ካላወጣ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ለሕይወትህ ዋጋ ስጥ (፫x)
የእድሜ ማራዘሚያው ነው ዋጋው ውድ
አስቀድመህ በመጠንቀቅ በመወሰን በመለወጥ
ዋጋህን ውድ አርገው የአንተን ማንነት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እንዴት ሰው እያወቀ (፪x)
እያወቀ ሁሉም አለቀ
እንዴት ሰው እየሰማ (፪x)
እየሰማ ምነው አልተስማማ
(ቢሰማ ግን) ይታቀብ ነበር
(ቢሰማ ግን) ይታመን ነበር
(ቢሰማ ግን) ይጠነቀቅ ነበር
(ቢሰማ ግን) ያመልጠው ነበር
ባጠገቡ ያለውን ሲያጣ
ከደጃፉ ሁሉም ሲቀጣ
ይህን አይቶ ምነው ቢመለስ
ተራው ዞሮ ለርሱ ሳይደርስ
እንዴት ሰው እያወቀ (፪x)
እያወቀ ሁሉም አለቀ
እንዴት ሰው እየሰማ (፪x)
እየሰማ ምነው አልተስማማ
(ቢሰማ ግን) ይታቀብ ነበር
(ቢሰማ ግን) ይታመን ነበር
(ቢሰማ ግን) ይጠነቀቅ ነበር
(ቢሰማ ግን) ያመልጠው ነበር
ባጠገቡ ያለውን ሲያጣ
ከደጃፉ ሁሉም ሲቀጣ
ይህን አይቶ ምነው ቢመለስ
ተራው ዞሮ ለርሱ ሳይደርስ
እንዴት ሰው እያወቀ (፪x)
እያወቀ ሁሉም አለቀ
እንዴት ሰው እየሰማ (፪x)
እየሰማ ምነው አልተስማማ
አዝማች · Chorus
የባህሪ ለውጥ አምጣ (፬x)
ከየት ይምጣ ከየት ይምጣ
ሰው ሁሉ ካለበት ሱስ ካልወጣ
ከየት ይምጣ ከየት ይምጣ
ሰው ሁሉ ደፍሮ እውነቱን ካላወጣ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ባህሪህም ያለው ስሜት ህም ያለው
ፈቃድህም ያለው በአንተ ውስጥ ነው
(ነው ነው ነው በአንተ ውስጥ ነው)
ባለቤቱ አንተ እንጂ ባህሪህ አይደለም
አለቃው እንተ ነህ ሌላ ማንም የለም
(የለም የለም ሌላ ማንም የለም)
አንተ ስትጸዳ አካባቢህ ይጸዳል
አንተ ስትለወጥ ባህሪህ ይለወጣል
(ይቀያየራል ሁሉም ይታደሳል)
(አዲስ ይሆናል ሕይወት ይጣፍጣል)
ተስፋ የቆረጠ ሊሞት ለመሰለ
ለሰው የሚራራ የሚለውጥ አለ
(አለ አለ ሰሚ ካለ የሚለወጥ ካለ
አለ አለ የሚለውጥ አለ) ፪x
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ