Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኦ እኔ ማነኝ

O Enie Manegn

2003 · ትራክ 1 · 6:51 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኦ እኔ ማነኝ

ቤቴስ : ምንድነው (፪x)

የሰማዩን ዜማ ዝማሬ

የፅድቅን ቅኔ አውቄ ተምሬ

እንድኖር ልብህ የፈቀደው

አምላክ ሆይ እኔ ማነኝ

ቤቴስ ምንድነው (፪x)

አውቃለሁ የእኔ ማንነቴን

የትውልድ ሐረግና ቤቴን

ለዚህ ልታበቃኝ የቻልከው

ካንተ የተነሳ ብቻ ነው

ይገርመኛል እስካሁን ድረስ

በቤትህ ቆሜ ስመላለስ

የተከልከኝ በቅዱስ ቃልህ

ስራህ ይደንቀኛል ምህረትህ

ኦ እኔ ማነኝ

ቤቴስ ምንድነው

የሰማዩን ዜማ ዝማሬ

የፅድቅን ቅኔ አውቄ ተምሬ

እንድኖር ልብህ የፈቀደው

ጌታ ሆይ እኔ ማነኝ

ቤቴስ ምንድነው (፪x)

ቅኔ ውሃ አይደል በነፃ

የሚቀዳ አይደለም ከጓዳ

የሚፈልቅ እንጂ ከሆዴ ውስጥ

የማይደርቅ አረከው እንደ ምንጭ

ሰው ፊት ዘመርኩ እንጂ ላንተ ነው

ምስጋና አምልኮ የማቀርበው

የምትቀበለኝ አንተ ነህ

ምርጫህ ተስማምቶኛል የእኔ ነህ

ኦ ጌታ ሆይ አመልክሃለሁ

ከመረጥከኝ ዘምሪ ብለህ

ልትሰማው ድምፄን ከፈለክ

ምስጋና አምልኮዬን ከወደድክ

በእውነት እና: በመንፈስ ሆኜ

ላምልክህ ላክብርህ ቆሜ ውዱ ጌታዬ (፪x)

መለወጤን ሲያዩ በዓይናቸው

የቀደሞው እየታወሳቸው

ሁለት የሆንኩኝ መሰላቸው

የውስጤንስ ማን ባሳያቸው

የተከልከኝን እኔ አውቃለሁ

በፍቅርህ ገመድ ታስሬአለሁ

አልቆልኛል ከእንግዲህ በቃ

የፊት ነው እርምጃዬ ከአንተ ጋ

ኦ ጌታ ሆይ አመልክሃለሁ

ከመረጥከኝ ዘምሪ ብለህ

ልትሰማው ድምፄን ከፈለግክ

ምስጋና አምልኮዬን ከወደድክ

በእውነትና መንፈስ ላምልክህ ቆሜ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ