ገና
Gena
2005 · ትራክ 1 · 5:29 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ገና ገና ገና ገና ገና ገና (ገና ገና)
ገና ገና ገና አዎ ገና ገና
የእግዚአብሔር ሥራ መች አለቀና (በእኔ በእኔ በእኔ)
የእግዚአብሔር ሥራ መች አለቀና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እንዲሁ በዋዛ መሞት አለ ወይ (መሞት አለ ወይ)
ሰውስ ስላወራ መሞት አለ ወይ (የለም የለም የለም)
ስለ እኔ የሚሟገት አለ በሠማይ
አለ በሠማይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ክብሩን ሲጨምርብኝ
ሞገሱን ሲደርብብኝ
ፀጋውን ሲያበዛልኝ
ኢህንን ያየ ጠላቴ በእኔ ላይ ቀና
ሞቷል እያለ በከተማው ሲያወራ
እኔ ግን አለሁ ከአምላኬ ጋራ
እኔ ግን አለሁ ከጌታ ጋራ
በክብሩ ወጣሁ ከአባቴ ጋራ
በሞገስ ገባሁ ከአባቴ ጋራ
ኑሮዬም ሕይወቴም በእግዚአብሔር እጅ ናት (በእግዚአብሔር እጅ ናት)
እስትንፋሴም ሁሉ በእግዚአብሔር እጅ ናት (ናት)
ታሪኬ አላበቃም ዞር በል አንተ ጠላት
ዞር በል አንተ ጠላት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ክብሩን ሲጨምርብኝ
ሞገሱን ሲደርብብኝ
ፀጋውን ሲያበዛልኝ
ኢህንን ያየ ጠላቴ በእኔ ላይ ቀና
ሞቷል እያለ በከተማው ሲያወራ
እኔ ግን አለሁ ከአምላኬ ጋራ
እኔ ግን አለሁ ከጌታ ጋራ
በክብሩ ወጣሁ ከአባቴ ጋራ
በሞገስ ገባሁ ከአባቴ ጋራ
አዝማች · Chorus
ገና ገና ገና ገና ገና ገና (ገና ገና)
ገና ገና ገና አዎ ገና ገና
የእግዚአብሔር ሥራ መች አለቀና (በእኔ በእኔ በእኔ)
የእግዚአብሔር ሥራ መች አለቀና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ