Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ልዑልን መጠጊያ

Leulen Metegiya

2005 · ትራክ 8 · 7:30 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ልዑልን መጠጊያ ፣ መጠጊያ

ያደረገው ሰዉ ተማምኖ ይኖራል

የለም የሚያሰጋዉ (፪x)

ጌትዬን መጠጊያ ፣ መጠጊያ

ያደረገው ሰዉ ተማምኖ ይኖራል

የለም የሚያሰጋዉ (፪x)

ተስፋን የሰጠው የታመነ ነው (፫x)

እንደተናገርው እንዲሁ አረገው

እንዲሁ አረገው ፣ እንዲሁ አረገው (፪x)

እንደተናገርው እንዲሁ አረገው ፣ እንዲሁ አረገው (፪x)

እንደተናገርው ነው ለእኔ ያረገው ፣ ነው ለእኔ ያረገው (፪x)

አይመስለኝም ነበር ጌታ ያለው የሚፈጸም

ኑሮዬን ሕይወቴን ዞር ብዬ ሳየው

ይህ ሁሉ ይሁን እንጂ ያለው ግን ይሆናል

እርሱ መች እንደ ሰው ተናግሮ ዝም ይላል

ያለው ይፈፀማል ኤልሻዳይ ነው

ያለው ይፈፀማል (፪x)

ለእርሱ ምን ይሳናል (፪x)

ልዑልን/ጌትዬን መጠጊያ ፣ መጠጊያ

ያደረገው ሰዉ ተማምኖ ይኖራል

የለም የሚያሰጋዉ (፪x)

ተናግሮ ማድረግን እርሱ ብቻ ያውቃል

ታዲያ ወንድሜ ሆይ ጌታ ምን ብሎሃል

ጠብቀው ተስፋህን አትወላውል ጽና

የተናገረህን ሲፈፅም እንድታይ

ያለው ይፈፀማል ኤልሻዳይ ነው

ያለው ይፈፀማል (፪x)

ለእርሱ ምን ይሳናል (፪x)

ተስፋን የሰጠው የታመነ ነው (፫x)

እንደተናገርው እንዲሁ አረገው (፫x)

እንደተናገርው እንዲሁ አረገው ፣ እንዲሁ አረገው (፪x)

እንደተናገርው ነው ለእኔ ያረገው ፣ ነው ለእኔ ያረገው (፪x)

ተናግሮ ማድረግን እርሱ ብቻ ያውቃል

ታዲያ እህቴ ሆይ ጌታ ምን ብሎሻል

ጠብቂው ተስፋህን አትወላውይ ጽኚ

የተናገረሽን ሲፈፅም እንድታዪ

ያለው ይፈፀማል ኤልሻዳይ ነው

ያለው ይፈፀማል (፪x)

ለእርሱ ምን ይሳናል (፪x)

ልዑልን/ጌትዬን መጠጊያ ፣ መጠጊያ

ያደረገው ሰዉ ተማምኖ ይኖራል

የለም የሚያሰጋዉ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ