ክብርህን ላውራ
Kebrehen Lawra
2005 · ትራክ 4 · 3:54 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የቱን ጀምሬ የቱን ልተወው
ይሄ ጌታ ለእኔ ያደረገው
ያደረገውን ሳስበው ሳስበው
ከቁጥር በላይ ነው
ለእኔ የሆነውን ሳስበው ሳስበው
ከቁጥር በላይ ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤት በአንተ ስንቱን አለፍኩኝ
የጠላቴን ጉልበት ረገጥኩኝ
ጌታ ለአንተ ምን ይሳንሃል
የጠላት ምሽግ ገና ይፈርሳል
ክብርህን ላውራ ዛሬም ነገም
የእስራኤል ቅዱስ አንተው ተባረክ
ብዙ ስራዬን አንተ ሰርተሃል
አመልክህ ዘንድ ይገባኛል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአንተ በአንተ በሆነው ነገር
እዚህ ደረስኩ ሥምህ ይባረክ
ደስታዬ ይኸው ፍፁም ሆነልኝ
አማኑኤል ክበርልኝ
አዝማች · Chorus
የቱን ጀምሬ የቱን ልተወው
ይሄ ጌታ ለእኔ ያደረገው
ያደረገውን ሳስበው ሳስበው
ከቁጥር በላይ ነው
ለእኔ የሆነውን ሳስበው ሳስበው
ከቁጥር በላይ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ