Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከመወለዴ ጀምሮ

Kemeweledie Jemero

2005 · ትራክ 10 · 8:12 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከመወለዴ ጀምሮ የማውቀው መልካም አንድ ነው

ከልጅነቴ ጀምሮ የማውቀው መልካም አንድ ነው

እርሱም አንተን ነው (፫x)

ጌታ መልካም ነው

አምላኬ አምላኬ እንዳንተ ያለ ማነው (፪x)

ኢየሱስ ሥልጣንህ ገደብ የለው

ኢየሱስ መንግሥትህ ፍጻሜ የለው

በዙፋንህ ፀንተህ ጥንትም ነበርክ

ዛሬም በክብር አለህ

ለዘለዓለም ደግሞ በሥልጣንህ

ገና ትኖራለህ

ከሁሉም በላይ ነህ የኔ ጌታ፣

ሁሉን ትገዛለህ

የሚወዳደርህ አቻ የለህ፣

አንተ እጅግ ታላቅ ነህ

አምላኬ አምላኬ እንዳንተ …..

ሀይልህ አያረጅም ክንድህ አይደክምም መች ትታክታለህ

የትላንቱ እግዚአብሔር አልተለወጥክ ዛሬም እግዚአብሔር ነህ

ጥንት የሰራኸውን አምላኬ ሆይ ዛሬም ሰርተኸዋል

በሀይለኛው ክንድህ አሸንፈህ ጠላቴን ረግጠሀል

አምላኬ አምላኬ እንዳንተ …..

ሰምቼ ነበረ በጆሮዬ :ጌታ ማዳንህን

ለብዙዎች ጥላ የማምለጫ አለት መሆንህን

በእውነትም አዳኝ ነህ መድሃኒቴ እኔም አይቻለሁ

ከዚህ ከጨለማ ከሞት መንደር በአንተ አምልጫለሁ

ጌታ እንዳንተ መልካም፣ ጆሮዬም አልሰማም፣

ጌታ እንዳንተ መልካም፣ አይኖቼም አላዩም፣

ጌታ እንዳንተ መልካም፣ ከቶ አልገጠመኝም፣

ለዘላለም ክበር፣ ከፍ በልልኝ(፪x)

እንዳንተ የሚሆን ለኔ የለም፣

አንተ ልዩ ከሁሉ ከላይ ነህ፣

አልፋና ኦሜጋ የኔ ጌታ፣

ዘላለም በክብር ምትበረታ

አልፋና ኦሜጋ አቻ የለህ

ዘላለም በክብር ትኖራለህ

ከመወለዴ ጀምሮ ….

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ