Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሁሉም በእርሱ ነው

Hulum Besu New

2005 · ትራክ 3 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሁሉም በእርሱ ነው (፪x)

ለእኔስ የሆነዉ

የሆነው ሁሉ የሆነዉ የሆነዉ

ሁሉም በእርሱ ነው (፫x)

እግዚአብሔር አምላኬ ሆዪ

ለእኔስ ያደረከውን ነገር ሳስበው (፬x)

ቆጥሬ አልዘልቀው (፪x)

በኢየሱስ ለእኔ ያደረከው አቤት የሚያስገርመው

ከሞት ከጥፋት ነጥቆ አኖረኝ ሕይወት ሰጥቶ

ስለዚህ በደስታ ላክብረው ይህን ጌታ

መልካሙን አዲስ ቅኔ ለሆነልኝ መድሃኒቴ (፪x)

ሁሉም በእርሱ ነው (፪x)

ለእኔስ የሆነዉ

የሆነው ሁሉ የሆነዉ የሆነዉ

ሁሉም በእርሱ ነው (፫x)

ሁሉም በእርሱ ነዉ ለእኔስ የሆነዉ (፬x)

ተቅበዝባዥ እረፍት ያጣሁ አሁን ግን በአንተ ረጋሁ

በሰላም መውጣት መግባት ሆነልኝ በዝቶ ምህረት

በለምለም መስክ ለመራኝ ከመንፈሱን ላጠጣኝ

መልካሙን ቅኔ ልቀኝ ጌታዬ/ኢየሱሴ እንካ ተቀበለኝ(፪x)

ሁሉም በእርሱ ነው (፪x)

ለእኔስ የሆነዉ

የሆነው ሁሉ የሆነዉ የሆነዉ

ሁሉም በእርሱ ነው (፫x)

ሁሉም በእርሱ ነዉ ለእኔስ የሆነዉ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ