Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በአንተ የታሰበ

Bante Yetasebe

2005 · ትራክ 9 · 4:13 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሠማያቶች ይስሙ ፣ ይስሙ ምድር ታስተጋባ

የምቀኘውን ቅኔ ያለኝን ምሥጋና

የከንፈሬን ፍሬ ፣ ፍሬ በፊቱ ላፍስሰው

ትናንት እንዳዜምኩት ደስታዬ በአንተው ነው

በአንተ የታሰበ የተረዳ ሰው

ጌታ እንደ እኔ ማነው (፪x)

እንደ እኔ ማነው ክብር ያየው

እንደ እኔ ማነው ወግ ያየው

እንደ እኔ ማነው ደስ ያለው

እንደ እኔ ማነው ክብር ያየው

እንደ እኔስ ማነው ወግ ያየው (፪x)

በሄድኩበት ሁሉ ፣ ሁሉ ስለ አንተ አወራለሁ

ስላደረክልኝ ድንቅ ቆሜ ዘምራለሁ

ከአደረከው አንዳች ፣ አንዳች አልጐደለብኝም

ምርጫዬ ነህ አንተስ እስከ ለዘለዓለም

በአንተ የታሰበ የተረዳ ሰው

ጌታ እንደ እኔ ማነው (፪x)

እንደ እኔ ማነው ክብር ያየው

እንደ እኔስ ማነው ወግ ያየው (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ