አበቃ
Abeqa
2005 · ትራክ 6 · 5:03 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አበቃ አከተመ በተባለ ጊዜ
ማነው ለእኔስ ፈጥኖ የደረሰው (፪x)
ጌታ እኮ ነው
ጌታ እኮ ነው አሃ (፫x)
ጌታ እኮ ነው
ይህን ያደረገው
ቁጥር 1 · Verse 1
እስራቴን ፈተህ ቀንበሬን ሰብረህ
ያስጨነቀኝ ጠላት ከእግሬ ሥር ጥለህ
ዛሬማ ቀና አልኩኝ ይኸው በኢየሱስ
ዘለዓለም ልገዛ ልስገድልህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አምላክ እንደሌለው ለምን አዝናለሁ
ረዳት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ
አባት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ
ረዳት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ
ሲረዳኝ በዓይኔ እያየሁ
ሲያግዘኝ በዓይኔ እያየሁ (፪x)
ሥምህን ጠርቼ ሁሉን አለፍኩ
መቼ አንተን ይዤ እኔስ አፈርኩ
ዛሬም የሚያቅተኝ ሁሉ
እወጣዋለሁ የአንተ ነው ኃይሉ (፪x)
አዝማች · Chorus
አበቃ አከተመ በተባለ ጊዜ
ማነው ለእኔስ ፈጥኖ የደረሰው (፪x)
ጌታ እኮ ነው
ጌታ እኮ ነው አሃ (፫x)
ጌታ እኮ ነው
ይህን ያደረገው
ቁጥር 3 · Verse 3
አምላክ እንደሌለው ለምን አዝናለሁ
ረዳት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ
አባት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ
ረዳት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ
ሲረዳኝ በዓይኔ እያየሁ
ሲያግዘኝ በዓይኔ እያየሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ