ጌታ እኮ ነው
Gieta Eko New
ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ እኮ ነው የሚባርከኝ
ጌታ እኮ ነው የሚያድርግልኝ
ጌታ እኮ ነው የሚደርስልኝ
ጌታ እኮ ነው የሚመጣልኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
እስኪቀደድ እስኪያፈስ መረቤ
የባረከኝ ተገኝቶ አጠገቤ
ባለቀለት ባበቃው ነገር ላይ
አደረገኝ ትንሳኤውን እንዳይ
ባከተመው በሞተው ነገር ላይ
አደረገኝ ትንሳኤውን እንዳይ
አዝማች · Chorus
ጌታ እኮ ነው የሚባርከኝ
ጌታ እኮ ነው የሚያድርግልኝ
ጌታ እኮ ነው የሚደርስልኝ
ጌታ እኮ ነው የሚመጣልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ እኮ ነው አታዩትም ወይ
የባረከኝ ከአቅሜ በላይ
ልጐትተው አልቻልኩትምና
ጓደኞቼ እርዱኝ ተገኙና
ልሸከመው አልቻልኩትምና
ወዳጆቼ እርዱኝ ተገኙና
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ እኮ ነው የሚያሳካልኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ጌታ እኮ ነው የሚያቃናልኝ
ጌታ እኮ ነው ያትረፈረፈኝ
ጌታ እኮ ነው ያረሰረሰኝ
እዛጋ ጣዪው መረቡን ሚለኝ
አሄ ብዬ መረቤን ጣልኩኝ
በበረከቱ አስደነገጠኝ
ይሄን ሁሉ መቼ ጠበኩኝ
በበረከቱ አስደነገጠኝ
ይሄን ሁሉ መቼ ጠበኩኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
ጌታ እኮ ነው ክብር የሰጠኝ
ቁጥር 6 · Verse 6
ጌታ እኮ ነው ሞገስ የሰጠኝ
ጌታ እኮ ነው ውበት የሆነኝ
ጌታ እኮ ነው . (1) .
በረከቱን መቼ ላከልኝ
እርሱ ራሱ ነው መጥቶ የሰጠኝ
በሰው መጠቀም አላስፈለገውም
ኢየሱስ ነው ቤቴ የገባው
በሰው መጠቀም አላስፈለገውም
ጌታዬ ነው ቤቴ የገባው
ቁጥር 7 · Verse 7
ጌታ እኮ ነው የሚያሸልለኝ
ቁጥር 8 · Verse 8
ጌታ እኮ ነው የሚያዘንጠኝ
ጌታ እኮ ነው ያንቀባረረኝ
ላመስግነው ለቀቅ አድርጉኝ
ጌታ እኮ ነው የሚያሸልለኝ
ጌታዬ ነው የሚያዘንጠኝ
ጌታዬ ነው ሕይወት የሰጠኝ
ላመስግነው ለቀቅ አድርጉኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ