አቤቱ ውበትህ
Abietu Wubeteh
ትራክ 8 · 6:23 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤቱ ውበትህ እጅግ ያስደንቃል
የፊትህን ብርሃን ማን አይቶ ይቆማል
አምልኮና ስግደት ክብር ይገባሃል
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x)
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)
እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x)
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ነበልባል ዓይኖችህን
ያማረውን ፊትህን
የነጠረው እግርህን
እናውራው ውበትህን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አቤቱ ውበትህ እጅግ ያስደንቃል
የፊትህን ብርሃን ማን አይቶ ይቆማል
አምልኮና ስግደት ክብር ይገባሃል
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x)
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)
እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x)
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ነበልባል ዓይኖችህን
ያማረውን ፊትህን
የነጠረው እግርህን
እናውራው ውበትህን (፪x)
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x)
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)
እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x)
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ምሥጋናም ሲያንስህ ነው
ዝማሬም ሲያንስህ ነው
አምልኮም ሲያንስህ ነው
ውዳሴም ሲያንስህ ነው
ካደረከው ጋራ ሳመዛዝነው
ከሰራኸው ጋራ ሳመዛዝነው
መልካምነቱን እናገራለሁ በጐነቱንም እዘምራለሁ (፪x)
ክብር ለሚገባህ ለአንተ ክብርን እሰጣለሁ
ስግደት ለሚገባህ ለአንተ ለአንተ እሰግዳለሁ
አምላኬ አከብርሃለሁ (፬x)
ቁጥር 6 · Verse 6
እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ ፤ ስላልተገኘ
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ ፤ ሊያይህ ተመኘ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ