አንተ ጌታዬ ነህ
Ante Gietayie Neh
ትራክ 7 · 5:57 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከፍ ከፍ ያልከው በዙፋንህ ላይ
አንተ አምላኬ አይደለህም ወይ
የገነንከው በማደሪያህ ላይ
አንተ ጌታ አይደለህም ወይ
አንተ ጌታዬ ነህ ኦሆሆ
አምላኬ ነህ ኦሆሆ ንጉሤ ነህ
ወደር የሌለህ ኦሆሆ (፪x) የሌለህ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ
አንተ አምላኬ ነህ ፤ አንተ ጌታዬ ነህ
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ
ዋጋዬን ሚከፍለኝ ወሮታዬ
ደሞዜን ሚሰጠኝ ሌት ቀለቤ
እግዚአብሔር አይደለም ወይ የሚያኖረኝ
እኔ ከእርሱ በስተቀር ጌታም የለኝ
እርሱ ጌታዬ ነው ፤ እርሱ ንጉሤ ነው
እርሱ አምላኬ ነው ፤ እርሱ ጌታዬ ነው
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ
አንተ አምላኬ ነህ ፤ አንተ ጌታዬ ነህ
አዝማች · Chorus
ከፍ ከፍ ያልከው በዙፋንህ ላይ
አንተ አምላኬ አይደለህም ወይ
የገነንከው በማደሪያህ ላይ
አንተ ጌታ አይደለህም ወይ
አንተ ጌታዬ ነህ ኦሆሆ
አምላኬ ነህ ኦሆሆ ንጉሤ ነህ
ወደር የሌለህ ኦሆሆ (፪x) የሌለህ
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ
አንተ አምላኬ ነህ ፤ አንተ ጌታዬ ነህ
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ
ቀድሞ ካደረክልኝ ይልቅ ዛሬ ያደረክልኝ በልጧል
ፍጥረት በመደነቅ ተሞልቶ አምላኳ እንዴት ወዷታል ይላል
ቀድሞ ካደረክልኝ ይልቅ አሁን ያደረክልኝ በልጧል
ፍጥረት በመገረም ተሞልቶ አምላኳ እንዴት ወዷታል ይላል
እንደንጋት ብርሃን ሙሉ ቀን እስኪሆን ይጨምራል ክብሩን
እንደንጋት ብርሃን ሙሉ ቀን እስኪሆን ይጨምራል ኃይሉን
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ (፪x)
አንተ አምላኬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ
ዋጋዬን ሚከፍለኝ ወሮታዬ
ደሞዜን ሚሰጠኝ ሌት ቀለቤ
እግዚአብሔር አይደለም ወይ የሚያኖረኝ
እኔ ከእርሱ በስተቀር ጌታም የለኝ
እርሱ ጌታዬ ነው ፤ እርሱ ንጉሤ ነው
እርሱ አምላኬ ነው ፤ እርሱ ጌታዬ ነው
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ
አንተ አምላኬ ነህ ፤ አንተ ጌታዬ ነህ
አዝማች · Chorus
ከፍ ከፍ ያልከው በዙፋንህ ላይ
አንተ አምላኬ አይደለህም ወይ
የገነንከው በማደሪያህ ላይ
አንተ ጌታ አይደለህም ወይ
አንተ ጌታዬ ነህ ኦሆሆ
አምላኬ ነህ ኦሆሆ ንጉሤ ነህ
ወደር የሌለህ ኦሆሆ (፪x) የሌለህ
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተ ጌታዬ ነህ ኦሆሆ
አምላኬ ነህ ኦሆሆ
ንጉሤ ነህ (፪x)
ወደር የሌለህ ኦሆሆ (፪x) የሌለህ
ወደር የሌለህ ኦሆሆ (፪x) የሌለህ
ወደር የሌለህ ኦሆሆ (፪x) የሌለህ
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ
አንተ አምላኬ ነህ ፤ አንተ ጌታዬ ነህ
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ (፪x)
አንተ አምላኬ ነህ ፤ አንተ ጌታዬ ነህ
አንተ ጌታዬ ነህ ፤ አንተ ንጉሤ ነህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ