ቅጥር ሰርተህ
Qeter Sertehe
ትራክ 9 · 5:50 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር መሪ ነው ሁሌ ይመራኛል
ከረግረግ ከጭቃ እኔን ያወጣኛል
እግሬን በሰላሙ መንገድ የሚያቀና
የታመነ አምላክ ይድረሰው ምሥጋና
አዝማች · Chorus
ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር መንፈስ ወደ እውነት መርቶኛል
በትዕዛዛትህ እንድሄድ አድርጐኛል
የቅዱሳንህን እግር የምትጠብቅ
በክንፎችህ ጥላ እኔን የምትደብቅ
አዝማች · Chorus
ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል
ቁጥር 3 · Verse 3
እርሱ የወደደው ተማምኖ ይኖራል
በትከሻው መሃል በክብርም ያድራል
እኔም ተወደድኩኝ ፍቅሩንም አየሁኝ
እግዚአብሔር ሳሳልኝ ተጠነቀቀልኝ
አዝማች · Chorus
ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ