Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቆሜ የምዘምረው

Qomie Yemezemerew

ትራክ 6 · 3:07 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዘምሬ ስወርድ: ሰው: ጎሽ እንዲለኝ

ስሜን አክብሮ እንዲያሞግሰኝ

ፍፁም አልሻም ደምቆ መታየት

ክብርህን ጋርዶ እራስን መግለጽ

እኔ ውርንጫ : ነኝ ጌታዬ ኢየሱስ ነው

እርሱን አክብሩልኝ ለእኔ ክብሬ ይሄ ነው

ኤፍታህ: ያለኝ ጌታ ለክብሬ አይደለም

እርሱን ላከብር እንጂ ልዘምር ዘለዓለም

መሳሪያ ድምጼን የማዋህደው

ጌታን ላከብር ተመስገን ልለው

አይደለም ለእኔ ክብሩ ለእርሱ ነው

በሕይወቴ ውስጥ አለኝ ውለታው

ቆሜ ምዘምረው ሱስ ይዞኝ አይደለም

ፍቅሩ አሸንፎኝ ነው ማርኮኝ ለዘለዓለም

ልምድ የለኝም ነበር የግጥም የዜማ

ግን ለኢየሱስ ክብር ይህ ሁሉ ተስማማ (፪x)

ሃሳቡን ይዤ ላገለግለው

የውን ሃሳቤ የእንቅልፍ ህልሜ ነው

ከብሮ በዓይኔ ሳይ ጠግቤ እረካለው

ምግብ አልሻም ሆዴን እረሳለሁ

ጌታ ሲከብርልኝ ዝለል ያሰኘኛል

ዘምር በእልልታ አመስግን ይለኛል

አመስግኜው ሁሌ እኔ አልጠግብምና

ገና እዘምራለሁ ወደ እኔ እስኪመጣ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ