ያ ሁሉ አለፈና
Ya Hulu Alefena
ትራክ 2 · 6:04 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እንደማያልፍ የለም ያሁሉ አለፈና
የሰቆቃው ዘመን በደስታ ተተካ አሜን
አንገቴን ደፍቼ የሰው ፊት ፈርቼ
ያለፍኩበት ዘመን ዘለፋ ጠግቤ አቤት
በቃ ሲለኝ ጌታ ወደ ገደል ገባ
የጐበጠ አንገቴ ለምሥጋና ቀና አሜን (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ምሥጋናዬ ይህ ነው ምሥጋናዬ
አሰዋለሁ ዛሬ በኮረብታ ቆሜ
ነጻ ወጥቼ ነጻ ሰው መሆን ችያለሁ
በክርስቶስ ዛሬ ትልቅ ተብያለሁ
የናቁኝም ያኔ አንቅረው የተፉኝ
ጐንበስ አሉ ጐንበስ ጌታ አክብሮኝ ሲያዩኝ
አዝማች · Chorus
እንደማያልፍ የለም ያሁሉ አለፈና
የሰቆቃው ዘመን በደስታ ተተካ አሜን
አንገቴን ደፍቼ የሰው ፊት ፈርቼ
ያለፍኩበት ዘመን ዘለፋ ጠግቤ አቤት
በቃ ሲለኝ ጌታ ወደ ገደል ገባ
የጐበጠ አንገቴ ለምሥጋና ቀና አሜን
ቁጥር 2 · Verse 2
አሁን ይኸው እንዲህ እንዲህ አምሮብኛል
አፌም በዝማሬ በዘይት ታብሷል
ማንም አልጠበቀኝ እኔን ለቁም ነገር
ጌታ ሲያረገው ግን ማነው የሚናገር
ምስኪኖች ሆይ በርቱ ጌታ አይጥላችሁም/ሰውን አይጥልም
ምስክር ነኝ እኔ በዓይኔ ስላየሁኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
እንደማያልፍ የለም ያሁሉ አለፈና
የሰቆቃው ዘመን በደስታ ተተካ አሜን
አንገቴን ደፍቼ የሰው ፊት ፈርቼ
ያለፍኩበት ዘመን ዘለፋ ጠግቤ አቤት
በቃ ሲለኝ ጌታ ወደ ገደል ገባ
የጐበጠ አንገቴ ለምሥጋና ቀና አሜን
ቁጥር 3 · Verse 3
ያኔ ያሰብኩት ሁሉ ወደ ገደል ገብቷል
አሁን በሕይወቴ ዛሬ አካሌ ቆሟል
ወገኖችም በቃ ብለው ነበር በቃ
በሃያሉ ኢየሱስ ከመቃብር ወጣሁ
እግሬም እንደዋላ አግሮች በርትተዋል
አፌም በዝማሬ በዘይት ታብሷል
አዝማች · Chorus
እንደማያልፍ የለም ያሁሉ አለፈና
የሰቆቃው ዘመን በደስታ ተተካ አሜን
አንገቴን ደፍቼ የሰው ፊት ፈርቼ
ያለፍኩበት ዘመን ዘለፋ ጠግቤ አቤት
በቃ ሲለኝ ጌታ ወደ ገደል ገባ
የጐበጠ አንገቴ ለምሥጋና ቀና አሜን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ