Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

Tesfaye Chala/Bamare Qenie/Fiteh Endetsehay Yaberal

ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፊትህ እንደ ፀሐይ ያበራል

እንደብዙ ውሆች ድምጽህም ያስፈራል

ግርማህ የደመቀ ሞገስህ ልዩ ነው

እግርህ ስር ወድቄ እሰግድልህ አለሁ

አልፋና ኦሜጋ የዘለዓለም ጌታ

ሞትን ድል ያደረክ: ኃጢአትን የረታህ

ከወገን ከቋንቋ ህዝቦችን የዋጀህ

ለአምላክህ መንግሥት ካህናት አድርገህ

(ሰባቱን መጽሃፍት ማህተም የፈታ

ውበትህ ያማረ የይሁዳ አንበሳ) (፪x)

ፊትህ እንደ ፀሐይ

ምስኪን ሆነህ መተህ ምስኪኑን ያከበርክ

ደሃ ሆነህ መተህ ደሃን ያበለጸክ

በደዌ ተመተህ ህምሙን የፈወስክ

ኃጢአትን ለብሰህ ሃጢያኑን ያነጻህ

(ድል ነስተህ በኃይልህ ባለድል ያረከን

አንተ አትጠገብም ኢየሱስ ተመስገን) (፪x)

ፊትህ እንደ ፀሐይ

ማምለጫ ቀዳዳ መሹለኪያ ሲጠፋ

ጐዳናው እጅግ ጠቦ ሰው ሁሉ ሲጋፋ

ችግር መፍታት አንተ ልማድህ ነውና

መጽሃፉን ገልጽህ ማኅተሙን ፈታህ

ጌታችን (ኢየሱስ) ተባረክ ባለግርማ ሞገስ

ዙፋንህ ከፍ ይበል በዓለም ሁሉ ንገሥ

ፊትህ እንደ ፀሐይ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ