Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምህረትህን አይቻለሁ

Meheretehen Aychalehu

ትራክ 7 · 6:33 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ውዴ (፫x) ኢየሱስ (፫x)

ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ

ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ (፪x)

አስራ ሁለት ዓመት ደም እየፈሰሰኝ

ተነጥዬ መኖር ሰው እንኳን እራቀኝ

ከእንግዲህስ ወዲያ ተስፋዬ ምንድን ነው

ዕድሜዬ በሙሉ በለቅሶ ሊያልቅ ነው

ብዬ ደምድሜ ሃሳቤን ስጠብቀው ፍጻሚዬን

ድንገት: ብርሃን: ወጣልኝ: አዳኜ ኢየሱስ መጣልኝ

ውዴ (፫x) ኢየሱስ (፫x)

ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ

ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ

ግርግሩ በዝቶ የሚጋፋው ሰው

አዳኜ ኢየሱስን እንዴት ላግኘው

ተስፋ ባለመቁረጥ እየተንፉቀኩኝ

እጄን ሰደድኩና ቀሚሱን ነካሁኝ

ነካ ባደርገው ነካኝ ኃይልም ወጣና ዳንኩኝ

ታዲያ ምን ልበል ይህን ጌታ አመስግኑልኝ በልልታ

ውዴ (፫x) ኢየሱስ (፫x)

ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ

ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ

ዘመናት አለፉ ሆኜ በጭንቀት

ለደሜ ማድረቂያ ጠፍቶ መድሐኒት

ማንም ማይጠጋኝ እርኩስ: ናት: ተብዬ

አሁንስ መረረኝ ገላግለኝ ጌታዬ

ብዬ ሞቴንም ስናፍቅ በሽታዬ: አርጎኝ: ድቅቅ

መሲሁ መጣልኝና አቆመኝ ፈወሰኝና

ውዴ (፫x) ኢየሱስ (፫x)

ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ

ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ

ትድናለች ብሎ ኧረ ማን ገመተኝ

ሁሉም በሩቅ ሲሸሽ ጀርባውን ሲሰጠኝ

አስታማሚ አጥቼ የምደግፈኝ

ኢየሱስ ሲጐበኘኝ በዛ ሚያጅበኝ

የሸሹኝ ሁሉ አቀፉኝ የናቁኝ ሁሉ አከበሩኝ

መሸማቀቄም ቀረልኝ ኢየሱስ ይመስገንልኝ

ውዴ (፫x) ኢየሱስ (፫x)

ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ

ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ

ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ