ሥምህ ይባረክ ለዘለዓለም
Semeh Yebarek Zelealem
ትራክ 10 · 7:19 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ለቅሶውን የሚሰማው አጥቶ ከሰው ህሊና ተረስቶ
ደክሞ በዓልጋ እየማቀቀ ዕድሜው ዘመኑ አለቀ
የተባለው ያ ሰው ዛሬ ይሄው ቆሟል
አስኪ እዩት አልጋውን በትከሻው ይዟል
ይህን የአደረገው ክብሩ የገነነ
ኢየሱስ ይባረክ ደሃን የተለመነ
አዝማች · Chorus
ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አሳዳጅ እጅግ ጨካኝ ሰው
አገር ምድሩ ሁሉ የሚያወቀው
ጌታን እምርሮ ሚጠላ ለሕግ: ከልቡ የቀና
ድንገት ጌታ ደርሶ ይህን ሰው ሲነካው
ሥሙ ጳውሎስ ሆነ ከዚያ ማን ይቻለው
ወንጌልን በምድር በስልጣን ሰበከ
ጀግና ነው ኢየሱስ ጀግናውን ማረከ
አዝማች · Chorus
ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አፈር ለብሶ የሸተተ ህይወቱ ኑሮው ተከተተ
አልዓዛር ወየው በቃለት ከኃጢአት ተለየ በሞት
ስትል ማሪያም አዝና እንባዋን እየዘራች
ምነው ኢየሱስ በዚህ ቢኖር ኖሮ እያለች
ተስፋ ቆርጣ ደክማ አልዓዛርን ጠራው
ኢየሱስ በዚያ ሲደርስ የድል ብርሃን በራ
አዝማች · Chorus
ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በመንገድ ወድቆ ሲለምን አካሉ ሁሉ ሲባክን
ሰርቶ: ወይ: ደክሞ አይበላ
ዘመኑን ሁሉ ሲጉላላ
ቀኑ ደረሰና ኢየሱስ መጣለት
ደጋግሞ እየጮኸ ተጣራ በእምነት
የለማኙን ጩኸት: ለይቶ: አደመጠ
ኢየሱስ ጌታ ነው ታሪኩን ለወጠ
አዝማች · Chorus
ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
በሃኪም ገንዘቧን ጨርሳ
ሃፍረት እንደ ሸማ ለብሳ
ከሰው ከሃገሩ እየራቀች
አስራ ሁለት ዓመት ማቀቀች
የምስኪኖች ተስፋ በመንደሩ አለፈ
ሊጐበኛት ፈቅዶ ሸክሟን አሳረፈ
ኧረ ምን ይባላል ምንስ ይመለሳል
እውነትም ፍቅር ነው ለምስኪን ይደርሳል
አዝማች · Chorus
ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (፪x)
ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ
ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ