ጻድቅ ግን በእምነት
Tsadeq Gen Bemnet
ትራክ 9 · 3:40 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ
ኖህ በምድረ በዳው መርከብን አበጀ
አብረሃም እርስቱን ከነዓንን ወረሰ
ሳራም በእምነቷ ኃይሏ ተመለሰ
አዝማች · Chorus
ጻድቅ ግን በእምነት በሕይወት ይኖራል
የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን ይረዳል
የተስፋውን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና
ደካሞች በእምነት ጉልበታችሁ ይጽና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ነፍሱ ፍፁም ደክማ ትንፋሽ ተሰውሮ
የሚታይ መመኪያ ከአፈር ተቀብሮ
ሥጋ ደግሞ ዝሎ ሞት ሽታ ሲሸተው
ጻድቅ ግን በእምነት ከክርስቶስ ጋር ነው
አዝማች · Chorus
ጻድቅ ግን በእምነት በሕይወት ይኖራል
የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን ይረዳል
የተስፋውን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና
ደካሞች በእምነት ጉልበታችሁ ይጽና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ባሕሩን በበትር አሻግሮ የከፈለ
ውሃን እንደ ግድግዳ ገትሮ ያቆመ
ዝናብን ኤልያስ በእምነት ከለከለ
እስራኤል በአምላኩ ጉልበቱ አየለ
አዝማች · Chorus
ጻድቅ ግን በእምነት በሕይወት ይኖራል
የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን ይረዳል
የተስፋውን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና
ደካሞች በእምነት ጉልበታችሁ ይጽና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ