Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እረኛን ይቀባል

Eregnan Yeqebal

ትራክ 8 · 6:27 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሳሙኤልም ወደ ሳኦል መጣ

ሳኦልም አንተ ለእግዚአብሔር የተባረክ ሁን

የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ፈጽሜአለሁ አለው

ሳሙኤልም ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጐች ጩኸትና

የበሬዎች ግሳት ምንድን ነው? አለ

ሳኦልም ህዝቡ ለአምላክህ ይሰውአቸው ዘንድ

መልካሞቹን በጐችና በሬዎችን አድነዋቸዋልና

አማሌቃዊያንም አምጥተዋቸዋል

የቀሩትንም ፈጽመን አጠፋን አለው

ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ

እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሳኦልን ስላነገሠ ተጸጸተ

እስከመቸ ድረስ ለሳኦል ታለቅሳለህ

ውረድ ቤተልሔም በቀንድ ዘይት ሞልተህ

ከልጆቹ መሃል አዘጋጅቻለሁ

ወደ እሰይ ቤት ግባ ንጉስ: እቀባለሁ

ሲለኝ አግዚአብሄር ፈራሁ ተደናገጥሁ

ሳኦል እንዳይሰማ ብዬ እጅጉን ፈራሁ

አንዲት ጊደር ይዤ ጌታዬ እንዳዘዘኝ

ጠራሁት እሰይን ልጆቹን እንዲያሳየኝ

በእውነት መልኩ ያማረ ቁመናው ሸበላ

ወደእኔ የተጠጋ ኤልያብ ነው ለካ

እግዚአብሔር ሚቀባው በፊቴ ይህ አለ

ለእስራኤል ንጉሥ ኧረ እፎይ ተገኘ

ብዬ በውስጤ አስቤ ልቀባው ስጠጋ

እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ አትቸኩል በል ረጋ

ሰው ፊትን እንደሚያይ እኔ አላይምና

በዓይኔ ፊት ቀሏል አልያብን አትቀባ (፪x)

ሌሎችም ሰባቱ አለፉ በፊቴ

እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ አልመረጥኩም እኔ

ልጆቹም አለቁ ማን ይሆን የቀረው

የሚቀባው የታል: ሰዉን: ግራ ገባው

የቀረ የለም ወይ እነዚሁ ናቸው

እስኪ እሰይ ልጆችህን በደንህ ቁጠራቸው

ገና ታናሽ አለ በጐች የጠብቃል

አለኝ መለሰና ሥሙ ዳዊት ይባላል (፪x)

ተጠርቶ መጣና በእኔ ፊት ቆመ

እግዚአብሔርም አየው ዓለኝ ቀባው ሂደህ

የአምላኬ መንፈስ ወደደው አረፈበት

ዳዊት ያ እረኛው በእውነት አማረበት

እግዚአብሔር ለካስ መቼ ፊትን ያያል

ልቡን ከወደደ እረኛን ይቀባል

እኔም ታሪክ አለኝ የዳዊትን መሳይ

አምላኬ ከትቢያ ከአመድ ላይ ሲያነሳኝ

እግዚአብሔር ለካስ መቼ ፊትን ያያል

ልቡን ከወደደ ምስኪኑን ያከብራል

እኔም ታረክ አለኝ የዳዊትን መሳይ

አምላኬ ከትቢያ ከአመድ ላይ ሲያነሳኝ

በሰው ዓይን ሲታዩ ዓይን የሚሞሉ

ትከሻቸው ሰፊ ቁመናቸው ብቁ

አልጠፉም ብዙ አሉ አገሩን ሞልተዋል

በጊዜ . (3) . እንጂ ታዲያ መች ከብረዋል

ለምን እንደወደደኝ በውል ባይገባኝም

ስለእራሴ ማውቀው ውብ ታሪክ የለኝም

እንደ እስራኤል በዕፍረት ነበርኩ እራቁቴን

ኢየሱሴ መጥቶ ጠጋ ባያለብሰኝ (፪x)

እግዚአብሔር ለካስ መቼ ፊትን ያያል

ልቡን ከወደደ እረኛን ይቀባል

እኔም ታረክ አለኝ የዳዊትን መሳይ

አምላኬ ከትቢያ ከአመድ ላይ ሲያነሳኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ