ርዕስ -
Title
ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው ጌታ ሆይ
መልካም መዓዛ አለው ውዴ ሆይ
መልካም መዓዛ አለው ጌታ ሆይ
ስምህን ጠርተን ተፈውሰናል
ካለብን ደዌ ነጻ ወጥተናል
ጅማታችንን ስምህ አራሰው
ልባችን ሞልቷል ሃሌሉያ ነው
ስለዚህ ጌታ ተመስገንልን
አዝማች · Chorus
አፍቅረንሃል ከውስጥ ከልብ
ጎልማሳነታችንም ታድሷል
በስምህ ብርታት ነጻ ወጥተናል
አይምሮ አርሶ ከልብም አልፎ
ያለ ሁኔታ ተድላን አልብሶ
የሚጣፍጠው ሥምህ ቁልፍ ነው
ደናግል ለአንተ በፍቅር ናቸው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሌሊት በምሽት ከእንቅልፍ ተነስተን
ስንበረከክ አንተን ፈልገን
ስምህን ጠርተን እፎይ እረካን
ኢየሱስ ጌታ ማን ይመስልሃል
ማድጋችንን ዘይትህ ሞላው
ያንን ስምህን ታምነን ስንጠራው
ባዶ ነበር ማስሮ ዕቃችን
ግን አሁን በአንተ አገኘን
ለጎረቤትም ተርፏል ሰላምህ
ከእኛም አልፎ ከደናግልህ
አዝማች · Chorus
ኦ ምንልህ የምንሰጥህ
የለንምና ከፍ ይበል ስምህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ