አባናና ፋርፋ
Abanana Farfa
2004 · ትራክ 1 · 6:05 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የእኔ ኢየሱስ ለየት ያለ መድሃኒት ነው
እርሱን ይዤ አሰቃዬን ከየት ላገኘው (፪x)
የለም አጣሁት የለም ፣ የለም ፈለኩት የለም
ጌታዬ ይክበር ለዘለዓለም ፣ ኢየሱሴ ይክበር ለዘለዓለም
ቁጥር 1 · Verse 1
ይፈውሳል ሲባል ሰማሁና ፈጥኜ ከቤቱ መጣሁና
ቃሌን አድርግ ብሎ ተዕዛዝ ሲያዘኝ
የመዳኔን መንገድ ሲጠቁመኝ
አላልኩም አባናና ፋርፋ ፣ አልሄድኩም ወደዚያ ልጠፋ (፪x)
አልቻልኩትም ብሎ አልጻፈም መሸኚያ (አሃሃሃ ሃሃ ሃሃሃ)
ኢየሱስ ብቻ ነው የፈውሴ መገኛ (አሃሃሃ ሃሃ ሃሃሃ) (፪x)
ባለመድሃኒት መድሃኒተኛ (፬x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ኢየሱስ ለየት ያለ መድሃኒት ነው
እርሱን ይዤ አሰቃዬን ከየት ላገኘው (፪x)
የለም አጣሁት የለም ፣ የለም ፈለኩት የለም
ጌታዬ ይክበር ለዘለዓለም ፣ ኢየሱሴ ይክበር ለዘለዓለም
ቁጥር 2 · Verse 2
ከኖርኩበት መንደር በድንገት ወጥቼ
የጠፋውን ነገር ፈልጌ አጥቼ
የልቤን መሻት ቢነግረኝ አልኩና
ከኢየሱሴ መንደር ድንገት ብቅ አልኩና
አላሰብኩም አልገመትኩም የሆነልኝ ነገር
ሲያንስበት እኮ ነው የእኔ መዘመር
ይፈውሳል ሲባል ሰማሁና ፣ ፈጥኜ ከቤቱ መጣሁና
ቃሌን አድርግ ብሎ ተዕዛዝ ሲያዘኝ
የመዳኔን መንገድ ሲጠቁመኝ
አላልኩም አባናና ፋርፋ ፣ አልሄድኩም ወደዚያ ልጠፋ (፪x)
አልቻልኩትም ብሎ አልጻፈም መሸኚያ (አሃሃሃ ሃሃ ሃሃሃ)
ኢየሱስ ብቻ ነው የፈውሴ መገኛ (አሃሃሃ ሃሃ ሃሃሃ) (፪x)
ባለመድሃኒት መድሃኒተኛ (፬x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ኢየሱስ ለየት ያለ መድሃኒት ነው
እርሱን ይዤ አሰቃዬን ከየት ላገኘው (፪x)
የለም አጣሁት የለም ፣ የለም ፈለኩት የለም
ጌታዬ ይክበር ለዘለዓለም ፣ ኢየሱሴ ይክበር ለዘለዓለም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ