ከምድረ በዳ
Kemedre Beda
2004 · ትራክ 2 · 5:42 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከምድረ በዳ ከሩቁ ጠርቶ
ልጁ አደረገኝ መንፈሱን ሰጥቶ ጌታ
ከምድረ በዳ ከሩቁ ጠርቶ
አገልጋይ አደረገኝ በዘይት ቀብቶ ጌታ
አዝማች · Chorus
የቅባቱ ውፍረት ቀንበሬን ሰበረው (አሃሃ)
የተጫነኝንም ሸክም አወረደው (ኦሆሆ)
እስራቴን ሁሉ የፈቱ እጆቹ
የምለው የለኝም በእውነት ይባረኩ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የጐልያድን ቁመት የልብሱን ክብደት (አሃሃ)
አጥኚ አይደለሁም የእርሱን የጦር ስልት (ኦሆሆ)
ምንም አይደንቀኝም ጦሩና ጡሩሩ
ወድቆ ይከሰከሳል በፊት በግንባሩ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በእኔ ተማምኗል አስጥለዋለዉ
ስሜንም አውቋል ጋርደዋለሁ
አለና ጌታ በበቀል ወጥቶ
ጠላቴን ጣለው እራሱን መቶ
አዝማች · Chorus
የረሳኸኝ መስሎት ጭፍራውን ሰብስቦ (አሃሃ)
ውድቀቴን እንዲያዩ ወዳጆቹን ጠርቶ (ኦሆሆ)
ጣቱን ቀስሮ ጉድ እዩ ሲላቸው
እኔን አአሰብክና ሃፍረት አለበስከው እህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከምድረ በዳ ከሩቁ ጠርቶ
ልጁ አደረገኝ መንፈሱን ሰጥቶ ጌታ
ከምድረ በዳ ከሩቁ ጠርቶ
አገልጋይ አደረገኝ በዘይት ቀብቶ ጌታ
ቁጥር 5 · Verse 5
ፈርጠም ወፈር ያለ ኤልያብ እያለ (አሃሃ)
በሰው የተናቀን ዳዊት ይቀባ ያለ (ኦሆሆ)
መረሳቴን ሽሮ በኢየሱስ/በልጁ ያሰበኝ
ምትክ የማይኖረው ለኔስ አምላክ አለኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
በእኔ ተማምኗል አስጥለዋለዉ
ስሜንም አውቋል ጋርደዋለሁ
አለና ጌታ በበቀል ወጥቶ
ጠላቴን ጣለው እራሱን መቶ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ