አልከሰርኩም
Alkeserkum
2004 · ትራክ 3 · 6:24 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ
ብሷል ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ዝማሪዬ (፫x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ማን ጠርቶ አፈረብህ አንገቱን ደፋብህ
ቀና አልልም ብሎ ተሸማቀቀብህ
እኔስ አላየሁም ከቶ አልሰማሁም
ከፍ ከፍ አልኩ አንጂ አላሽቆለቆልኩም
ሲወራ ሰምቼ ነበረ አሁን ግን ዓይኔ አይቷል
ምሥጋናዬም ብሷል
አዝማች · Chorus
አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ
ብሷል ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ዝማሪዬ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እርሱማ ሞኝ ነው ጊዜውን ይፈጃል
ኢየሱስ ኢየሱስ ሲል ዕድሜውን ይገፋል
ቢሉኝ ከሰነፎች መንደር አንዳንዶቹ
እንግዲህ ማዳኑን ያያል ዓይናቹህ
በምድር መቶ እጥፍ በሰማይ የዘለዓለም ሕይወት
አለኝ በኢየሱስ ቤት
አዝማች · Chorus
አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ
ብሷል ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ዝማሪዬ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሞቅ ደመቅ ካሉ ከፈርዖን ቤት
በንጉሠ ነገሥት ስልጣን ካለበት
ጮማ ሲል ወይን ጠጅ ድሎት በሞላበት
ብድራቱን ቆጥሮ ሙሴ አድርጓል ለቀቅ
ለሁሉ እንደስራው ምትከፍል ነህና አምላኬ
አረፈብህ ልቤ
አዝማች · Chorus
አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ
ብሷል ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ዝማሪዬ (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እርሱማ ሞኝ ነው ጊዜውን ይፈጃል
ኢየሱስ ኢየሱስ ሲል ዕድሜውን ይገፋል
ቢሉኝ ከሰነፎች መንደር አንዳንዶቹ
እንግዲህ ማዳኑን ያያል ዓይናቹህ
በምድር መቶ እጥፍ በሰማይ የዘለዓለም ሕይወት
አለኝ በኢየሱስ ቤት
አዝማች · Chorus
አልከሰርኩም አላፈርኩም አንተን አንተን ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ዛሬ ብሷል ምሥጋናዬ
ብሷል ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ዝማሪዬ (፫x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ብሷል ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ዝማሪዬ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ