Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማን ጠገበ

Man Tegebe

2004 · ትራክ 4 · 5:44 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ማን ጠገበ (ዬ) ማን ረካ

ቃላት ቢደረደር በዝማሬ ተርታ

እኔ በበኩሌ አልረካሁም

አንተን የሚገልጥ ቃል አላገኘሁም

እንዲያውም ለክብርህ ባሉኝ ቃላቶቼ

ላደናንቅህ እንጂ መቅደስህ ገብቼ (፪x)

እንካ ጌታ ጣፋጭ ምሥጋናዬን

ስለአንተ ያለኝን ልግለጽ በዜማዬ (፪x)

ቃልህን ልከኸው በሕይወቴ ድንቅን ሰራ

ከፊቴ ተነሳ የገዘፈው ያ ተራራ

ታዲያ ለማመስገን ማን ከልክሎኝ ዝም እላለሁ

ከልካይ የለብኝም ተፈትቼ አመልካለሁ (፪x)

ሌላ (፬x) እንደአንተ ያለ የለም ሌላ (፪x)

የሚጤሰውን ጧፍ ሳታጠፋ ቅጥቅጡን ሸምበቆ ሳትሰብረው (፪x)

ድምጽን ሳታሰማ ትመጣለህ ፍጥረትን መገረም ትሞላለህ (፪x)

ልግባ ወደአንተ በአምልኮ

በዐይኔ አሳይቶኛል ክንድህ ድንቅ ሰርቶ

ተቀበለኝ ምሥጋናዬን

ውዴ ለአንተ ያለኝን ይህን ስጦታዬን

የአባቶች አምላክ ዘምርልሃለሁ

አፌን ብቻ አይደለም ልቤን እሰጥሃለሁ (፪x)

የሚጤሰውን ጧፍ ሳታጠፋ ፣ ቅጥቅጡን ሸምበቆ ሳትሰብረው (፪x)

ድምጽን ሳታሰማ ትመጣለህ ፣ ፍጥረትን መገረም ትሞላለህ (፪x)

ማን ጠገበ (ዬ) ማን ረካ

ቃላት ቢደረደር በዝማሬ ተርታ

እኔ በበኩሌ አልረካሁም

አንተን የሚገልጥ ቃል አላገኘሁም

እንዲያውም ለክብርህ ባሉኝ ቃላቶቼ

ላደናንቅህ እንጂ መቅደስህ ገብቼ (፪x)

ሌላ (፬x) እንደአንተ ያለ የለም ሌላ (፫x)

ሌላ (፪x) ሌላ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ