የወንጌል አርበኛ
Yewengiel Arbegna
2004 · ትራክ 7 · 4:47 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አርበኛ ነኝ (፪x) የወንጌል አርበኛ
ጌታም አድርጐኛል የእውነት ሰራተኛ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አልፈራ አልደነግጥ ልቤም አይሸበር
ጌታ ፍርሃቴን አድርጐታል ሰበር (አድርጐታል ሰበር)
ጉልበታም መንፈሱ በእኔ ላይ ተለቋል
ጠላቴ ይህን አይቶ ሁሌ ያንዣብባል
ይዙር ያንዣብ እንጂ ምኔን ያገኘዋል
(ይዙር ያንዣብ እንጂ ምኔን ያገኘዋል)
እኔን ሊነካ ሲል እሳት ይቀድመዋል (፪x)
አዝማች · Chorus
አርበኛ ነኝ (፪x) የወንጌል አርበኛ
ጌታም አድርጐኛል የእውነት ሰራተኛ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቅጥሬ የእግዚአብሔር ጦር ደሞዜ በሰማይ
ይሄ ስለሆነ ምንም ምንም አላይ (ምንም ምንም አላይ)
በሃይል ተሞልቼ በብርቱ እዋጋለሁ
ያዘዘኝን ጌታ ደስ ደስ ላሰኘው
አዝማች · Chorus
አርበኛ ነኝ (፪x) የወንጌል አርበኛ
ጌታም አድርጐኛል የእውነት ሰራተኛ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በጠቅላዩ ገዤ በኢየሱስ ታዝዤ
ወደጠላት መንደር በመንፈስ ገስግሼ (በመንፈስ ገስግሼ)
ጉድ ሳልሰራ አልመጣም በፍፁም በባዶ
አየዋለሁ ጠላት በእሳት ቆስሎ ነዶ
ይዙር ያንዣብ እንጂ ምኔን ያገኘዋል
(ይዙር ያንዣብ እንጂ ምኔን ያገኘዋል)
እኔን ሊነካ ሲል እሳት ይቀድመዋል (፪x)
ደግሞ ለጠላቴ እድል ፈንታ አልሰጥም
ከደሊላ ጭን ላይ ተኝቼ አልገኝም (አልገኝም)
የጌታዬ መንፈስ በእኔ ላይ ስላለ
እንደወደደው ያድርገኝ እርሱ እንደፈለገ
አዝማች · Chorus
አርበኛ ነኝ (፪x) የወንጌል አርበኛ
ጌታም አድርጐኛል የእውነት ሰራተኛ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ