Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዝም ብዬ

Zem Beyie

2004 · ትራክ 9 · 5:25 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዝም ብዬ (እህህ) ወደፊት (እህህ) እገሰግሳለሁ

የኋላዬን ትቼ የፊቴን እይዛለሁ (፪x)

እይዛለሁ (፪x) ለጦር ያስከተተኝ እርሱን ደስ ያሰኘው

እይዛለሁ (፪x) ለጦር ያስከተተኝ እርሱን ደስ ያሰኘው

1/ለነሰንበላጥ ለነጊሳም

ና ውረድ ለሚል ሥራ ሊያስቆም

ከንቱ ለሆነው ለዚህ ቃላቸው

አልንበረከክ ከቶ አልሰማቸው (፪x)

2/ለሥጋ ጥቅም ለነፍሴ ክሳት

እኔ አልለምንም በዚህስ ወራት

ለአምላኬ ደስታ እሆንለታለሁ

ብዙ ሥራ ነው ከፊቴ ያለው (፪x)

> ዝምብዬ (እህህ) ወደፊት (እህህ) እገሰግሳለሁ

የኋላዬን ትቼ የፊቴን እይዛለሁ (፪x)

እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ለጦር ያስከተተኝ እርሱን ደስ ያሰኘው

እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ለጦር ያስከተተኝ እርሱን ደስ ያሰኘው

3/ለይናቅ ልጆች ለነፊልሞች

በዐይን ሲታዪ ለረዣዥሞች

ወዬው እዬዬ ብዬ አልጮህም

እኔ የማመልከው ሽንፈት አያውቅም (፪x)

4/ድንቃ ድንቅ አድርጐ አንዴ ጠርቶኛል

የእውነትን መንገድ አሳይቶኛል: ቀብሬ ልምጣ ብዬ አልጠይቅም

ፍሬ ለሌለው ጊዜዬን አልፈጅም (፪x)

ዝም ብዬ (እህህ) ወደፊት (እህህ) እገሰግሳለሁ

የኋላዬን ትቼ የፊቴን እይዛለሁ (፪x)

እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ለጦር ያስከተተኝ እርሱን ደስ ያሰኘው

እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ለጦር ያስከተተኝ እርሱን ደስ ያሰኘው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ