አምላካችን
Amlakachen
2004 · ትራክ 10 · 4:48 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምላካችን መጠጊያችን ኃይላችን
ባገኘነው በታላቅ መከራ ረዳታችን (፪x)
ሆኖልናል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የማዳን ደስታ ለእኛ ሰጥቶን
በሽታ መንፈስ ይኸው ለውጦ
ከዚም የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም
ስለወዳጆቹ የሚሰጥ እራሱን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሄደን ነበር ወደ ተራራ
አይተን ነበር በብዙ አቅጣጫ
ተስፋ ሚሆን ቢታጣም በዚያ
አግኝተናል የዓይን ማረፊያ
የዓይኖቻችን ማረፊያ ጌታ
የዓይኖቻችን ማረፊያ ኢየሱስ
አዝማች · Chorus
አምላካችን መጠጊያችን ኃይላችን
ባገኘነው በታላቅ መከራ ረዳታችን (፪x)
ሆኖልናል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መች በቀላሉ ሚታለፍ ነበር
በሕይወታችን የሆነው ነገር
እርሱ/ጌታ ሲመጣልን ወጥመድ ተሰበረ
የተከሰስንበት እዳችን ተሻረ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሄደን ነበር ወደ ተራራ
አይተን ነበር በብዙ አቅጣጫ
ተስፋ ሚሆን ቢታጣም በዚያ
አግኝተናል የዓይን ማረፊያ
የዓይኖቻችን ማረፊያ ጌታ
የዓይኖቻችን ማረፊያ ኢየሱስ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ